ETH

ETH

ቲክቫህ ኢትዮጲያ

የሐረማያ ዮንቨርስቲ ማስተማር ካቋረጠ ከአንድ ወር በላይ እንደሆነው የዩኒቨርስቲዉ ሠራተኛ እና ተማሪዎች አስታወቁ ።

 «ከተመዘገብን አንስቶ እስካሁን በአግባቡ የተማርነው አንድ ሳምንት ቢሆን ነው» የሚለው አንድ የዩንቨርስቲው ተማሪ በዚሁ መስተጓጎል ምክንያት ወደ ቤተሰቦቹ ከተመለሰ አንድ ወር እንደሆነው ገልፆልናል። በስልክ ያነጋገርናቸዉ አንድ ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ የዩንቨርስቲው ባልደረባ እንደገለፁልን ደግሞ ትምህርት መልሶ ከተጀመረ 10 ቀን ገደማ ቢሆነውም ክፍል የሚገባው ተማሪ ቁጥር በጣም ውስን ነው። ለዚህም ባልደረባው በምክንያትነት የጠቀሱት አንዳንድ ተማሪዎች በድብቅ በሚያሰራጩት የማስፈራሪያ እና የአድማ ወረቀቶች ምክንያት ነው።

 «በሐሮማያ ዩንቨርስቲ ግጭት ከተቀሰቀሰ አንስቶ የከፋ ችግር  እንዳይከሰት ለመቆጣጠር ዩኒቨርስቲዉ ቅጥር ግቢ የሰፈረዉ የፌደራል ፖሊስ ቁጥር እንዲጨምር ተደርጓል ፣መከላከያም ገብቷል።  የኦሮሚያ አድማ በታኝ እና የዩንቨርስቲው ጥበቃም በግቢው ይገኛሉ» ተብሏል። በሐረማያ  ዮንቨርስቲ ግጭት የተጀመረው ጥቅምት መጨረሻ ወልዲያ ዩንቨርስቲ ሁለት ተማሪዎች ከመገደላቸው ጥቂት ቀናት አስቀድሞ ነው። የዩንቨርስቲው ተማሪዎች  ሰልፍ በመውጣት ወለጋ ላይ የተደነገገዉ የኮማንድ ፖስት አገዛዝ ይነሳ፣ መከላከያ ሠራዊት ከኦሮሚያ ይውጣ እና  ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከስልጣን ይውረዱ በሚል የፖለቲካ ጥያቄዎች አንስተው መንግሥት በአፋጣኝ ምላሽ ይስጠን ብለው ትምህርት አቁመው እንደነበር የዩንቨርስቲው ባልደረባ ተናግረዋል።

« በካፍቴሪያ ውስጥ ከዚህ ቀደም ከሚመገቡት 13000 ገደማ ተማሪዎች በአሁን ሰዓት  5000 ተማሪዎች ብቻ የሚገኙበት ሁኔታ አለ» ብለዋል የዮንቨርስቲው ባልደረባ።  

የተለያዩ የዩንቨርስቲ ፕሬዚዳንቶች አዲስ አበባ ውስጥ ትናንት እና ዛሬ በጋራ በተለያዩ ዮንቨርስቲዎች የተነሱትን ግጭቶች ተከትሎ በቀጣይ ሂደቱ ላይ በመምከር ላይ እንደሚገኙም ታውቋል።

Report Page