#eth

#eth


"አብሮነት ከጋሞ እስከ ጎንደር" የተሰኘ የጉዞ ፕሮግራምን በተመለከተ እና "የኢትዮጵያ የሀገር

ሸማግሌዎች ሕብረት" ምስረታን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ በአርባ ምንጭ ተሰጠ፡፡ 

የግንዛቤ ማስጨበጫውን ያዘጋጀው ሕብረመንጎል ቲቪ መልቲ ሚዲያ የተባለ የግል ድርጅት ሲሆን እስካሁን

በመንግስትም ሆነ በሌሎች አካላቶች እየተሰሩ ያሉትን የሠላም እና የእርቅ ሥራዎችን ለማገዝ እና የበኩሉን

አስተዋፅኦ ትውልዱ ላይ ለማሳረፍ ፣እንዲሁም ሃላፊነቱን ለመወጣት ይቅርታ፣ ፍቅርን ፣ መቻቻልን እና

መከባበርን ፣ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትና አንድነትን ለማጠናከር ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው በማመን ይህንን

"አብሮነት ከጋሞ እስከ ጎንደር" የተሰኘውን ሀገር አቀፍ የአብሮነት የጉዞ ዝግጅት ለየት ባለ ሁኔታ ከጋሞ ዞን

አርባ ምንጭ ተነስቶ የ6 የሀገራችንን ልዩልዩ ከተሞች አቆራርጦ በመሄድ የሁሉንም የኢትዮጵያ አካባቢዎች

የሀገር ሽማግሌዎች እና የወጣቶች ተወካዮችን በልዑካን ቡድን ውስጥ በማቀፍ እና በማካተት በመንገድ ጉዞ

አጋጣሚም በሚታረፍባቸው እና በሚታለፍባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችን ጭምር በመጎብኘት

ተማሪዎችን የማበረታታት እና የመምከር ተግባር አከናውኖ በመጨረሻም ለጥምቀት በዓል ወደ ታሪካዊቷ

ጎንደር ከተማ በመግባት ጉዞውን ከማጠናቀቁ በፊት "የኢትዮጵያ የሀገር ሸማግሌዎች ሕብረት" እንዲመሰረት

ታላቅ ጉባኤ በማድረግ በቀጣይነት ተመሳሳይ ግንኙነቶች እንዲካሄዱ የሚያስችል ኮሚቴ በማዋቀር

እንዲጠናቀቅ ዕቅድ ነድፎ እየተንቀሳቀስ እንደሚገኝ ድርጅቱ ገልጿል፡፡ 

ይህ የጉዞ ሀሳብ የቀዘቀዙትን ባህላዊ እሴቶቻችንን ይበልጥ ለማድመቅ እና የተዘነጉትን እና በውጭ

ጠላቶቻችን ሴራ እንዲደበዝዙ የተደረጉትን መልካም የሆኑ የእርቅ የሠላም የይቅርታ እና የባህላዊ የግጭት

አፈታት እሴቶቻችንን መልሰን ወደ ነበሩበት ሥፍራ ከማምጣት ባሻገር አሁን ላይ ላንዣበቡብን ዘር እና ብሔር

ተኮር ግጭቶች እና ደም አፋሳሽ ስጋቶች እንደ መፍትሔ ለመጠቀም እንዲያስችል በር ይከፍታል ተብሎ 

ይታሰባል ሲል ሕብረ መንጎል አስታውቋል፡፡ 

የፕሮግራሙዋና ዓላማ የኢትዮጵያዊነት እሴት እንዲዳብር ጥረት ለማድረግ እና የኢትዮጵያዊነትን የአብሮነት

ባህልን ይበልጥ በማዳበር የህብረተሰቡን በተለይ የወጣቶችን አመለካከት ለማሻሻል ዓላማ ያደረገ 150 

አባላትን በልዑካን ቡድንነት ያቀፈ የጉዞ ፕሮግራም ማድረግ እና "የኢትዮጵያ የሀገር ሸማግሌዎች ሕብረት" 

እንዲመሰረት መሰረት መጣል መሆኑ ታውቋል፡፡

የፕሮግራሙ ግብ ደግሞ በበለፀገች ኢትዮጵያ ውስጥ የኢትዮጵያውያንን የአብሮነት ባህል በማዳበር

"የኢትዮጵያ የሀገር ሸማግሌዎች ሕብረት" እንዲመሰረት መሰረት መጣል ነው ተብሏል፡፡ 

የሀገር ሽማግሌዎች ሕብረት ለመመስረት አሁን ጊዜው ግድ ይለናል ያለው ድርጅቱ በሀገራችን በተለያዩ

ቦታዎች ብሔር እና ዘር ተኮር ጥቃቶች እየተበራከቱ ከመምጣታቸውም በላይ በአንዳንድ አካባቢዎች

የግጭቶች መንስኤ መሆናቸውን እያየን እና እየሰማን ነው፡፡ለዚህ ችግር ዘላቂው መፍትሔ በተደራጀ መንገድ

ባሉን ጠንካራ ባህሎቻችን እና በእሴቶቻችን ተጠቅመን የግጭት መንስኤዎችን ከምንጩ ለማድረቅ ጥረት

ለማድረግ ነው ብሏል፡፡ 

ድርጅቱ የቆመለትን ስለ ኢትትዮጵያ የመትጋት ዓላማ እውን ለማድረግ በርካታ ዕቅዶችን በመንደፍ

በሀገራችን የሚዲያ እንቅስቃሴ ላይ አሻራውን ለማሳረፍ እና ለተግባራዊነቱም በውስጡ ባሉት ጋዜጠኞች እና

ባለሙያ ሠራተኞች እንዲሁም በአጋር አካላት ጭምር የኢትዮጵያዊነትን እሴቶች በመጠበቅ እና በሀገሪቱ

የሚፈጠሩ ችግሮችን በያገባኛል ስሜት ለመፍታት የዜግነት ግዴታውን ለመወጣት ጥረት የሚያደርግ ተቋም

ሲሆን በሚዲያው ዘርፍ ለሀገራችን የሚጠበቅበትን የዜግነት እና የተቋም ግዴታ እየተወጣ የሚገኝ ድርጅት

መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ 

 የሀገር ሽማግሌዎች እና የወጣቶች የኢትዮጵያዊነት እሴት እንዲዳብር እና የኢትዮጵያውያን የአብሮነት

ባህልን አንድም ወደ ቀደመ ሥፍራው ለመመለስ አንድም ይበልጥ በማዳበር ህብረተሰቡን ለማስተማር

እንዲቻል የበኩላችንን ጥረት ለማድረግ እንዲሁም ጠንካራ ማህበረሰብ በመፍጠር ሂደት ውስጥ ዋና ተዋናይ

በመሆን አዘጋጁ ሕብረመንጎል ቲቪ መልቲ ሚዲያ ኃ/የተ/የግ/ማ ድጋፍ በማድረግ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን

ያረጋግጣል ብሏል፡፡ 

Report Page