#ETH

#ETH


ለ14ኛ ጊዜ በአዲስ አበባ ከተማ የሚከበረው የኢትዮጰያ ብሔር ፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በሰላም እንዲከበር የፀጥታ አካለት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቀው ወደ ስራ መግባታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

““ህገ-መንግስታዊ ቃል ኪዳናችን ለዘላቂ ሰላም” ” በሚል መሪ ቃል ህዳር 29 ቀን 2012 ዓ/ም በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አዘጋጅነት 14ኛው የኢትዮጰያ ብሔር ፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በአዲስ አበባ ስታዲየም በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ይከበራል፡፡

በበዓሉ ላይ ለመታደም እንግዶች ወደ አዲስ አበባ እየገቡ መሆኑን ኮሚሽኑ ጠቁሞ በብሔራዊ ደረጃ በሚከበረውና በርካታ ህዝብ የሚታደምበት በዓል በሰላም እንዲከበር ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ፣ የኦሮሚያና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽኖች እንዲሁም ሌሎች ተቋማትን ያካተተ የፀጥታ ኮማንድ ፖስት ተዋቅሮ ስራ መጀመሩን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡

ህዝብ አሰታፊ የፀጥታ ስራ በመሰራቱና ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ትብብር በማድረጉ በያዝነው ዓመት ህዝብ በስፋት የተሳተፈባቸው ልዩ ልዩ ሃይማኖታዊ በዓላትና ዝግጅቶች በሰላም መከበራቸውን ኮሚሽኑ አስታውሶ የኢትዮጰያ ብሔር ፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ማንነታቸውንና አኩሪ ባህላቸውን በአደባባይ የሚያንፀባርቁበት የዘንድሮ በዓል የብሔር ፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በሰላም እንዲከበር ህብረተሰቡ የተለመደውን ትብብር እንዲያደርግ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጥሪውን አቀርቧል፡፡

ቀኑን አስመልከቶ በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚከናወኑ ልዩ ልዩ ስነ-ስርዓት ተጀምረው እስከሚጠናቀቅ ድረስ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር፡-

• ከሰንጋ ተራ ወደ ለገሃር

• ከሜክሲኮ አደባባይ በለገሃር ወደ አዲስ አበባ ስታዲየም

• ከብሔራዊ ቲያትር ወደ ለገሃር

• ከሀራምቤ ሆቴል ወደ ለገሃር

• ከሀራምቤ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ሲሆኑ፡-

ከፕሮግራሙ ዋዜማ ማታ ጀምሮ በአዲስ አበባ ስታዲዮም የሚካሄደው ስነ-ስርዓት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ በስታዲየም ዙሪያ እና አካባቢው በግራና ቀኝ ለረጅም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን ኮሚሽኑ እየገለፀ

ህብረተሰቡ ለጸጥታ አጠራጣሪ የሆኑ ነገሮች ሲያጋጥሙት ይሁን የፖሊስ አገልግሎት ለማግኘት በስልክ ቁጥሮች-

11-5-52-63-03 ፣

011-5-52-40-77 ፣

0115-52-63-02 ፣

011-1-11-01-11

ወይም በነፃ ስልክ መስመር 991 እና 987 መጠቀም እንደሚችል ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡ በመጨረሻም ኮሚሽኑ ለመላው የኢትዮጵያ ብሔሮች ፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓሉ የሰላም የደስታ እንዲሆንላቸው መልካም ምኞቱን ገልጿል፡፡

Report Page