#ETH

#ETH


በድጋሚ ለሀገራችን መንግስት ጥሪ እናቀርባለን!

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ያሉ እንቅስቃሴዎችን በንቃት ሲከታተል ቆይቷል። ተማሪዎች የሚያቀርቡትን ቅሬታዎች፣ ጥያቄዎች፣ የሚደርሱባቸው ችግሮችን በገፁ አማካኝነት ለሚመለከታቸው ሲያቀርብ ነበር። ከዛሬ ሁለት ዓመት በፊት የነበረው እንቅስቃሴ እና በዚህ ዓመት የተመለከትናቸው ፈፅሞ የሚገናኙ አይደሉም። መረጃዎች ሁሉ መልካቸውን የሚቀይሩበት፣ ነገሮች የሚቀጣጠሉበት ሁኔታም ከዚህ በፊት ገጥሞን አያውቅም።

ከዚህ ቀደም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በጋር ሆነው ችግሮቻቸው እንዲፈቱላቸው ሲተገሉ፣ ሢጠይቁ፣ ድምፃቸውን በጋራ ሲያሰሙ ነው የምናውቀው አሁን ግን እየተመለከትነው ያለነው ነገር እጅግ ተቃራኒው ነው። ይህ ጉዳይ ነገ ሳይሆን ዛሬ እልባት ካልተሰጠው ሀገሪቷን ከባድ ፈተና ውስጥ ይከታታል። በየዩኒቨርሲቲ ውስጥ ከህግ በላይ የሆኑ አካላት የሚያደርጉትን እንቅስቃሴዎች በዝምታ እየታለፈ፣ በሚዲያዎች እየቀርቡ የተዛቡ እና የተሳሳቱ መረጃዎች መስጠት ተማሪዎችን እና የተማሪ ወላጆችን እያስቆጣ ነው።

ውድ ቤተሰበቦቻችን ዛሬም የሚሰማን የመንግስት አካል ካለ እንጮሃለን፤ የት የት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተለይተው እንዳይማሩ እየተደረገ እንደሆነ፣ የት የት ዩኒቨርሲቲ ትምህርት እንደተቋረጠ፣ የትኞቹ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ተማሪዎች ማስፈራሪያ እንደሚደርሳቸው፣ በየትኞቹ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የማስጠንቀቂያ ወረቀቶች እንደልብ እንደሚሰራጩ፣ ከየትኞቹ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በስጋት ምክንያት በርካታ ተማሪዎች ግቢ ለቀው እንደወጡ፣ በየትኛው ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሚደርሳቸውን ማስፈራሪያ ምክንያት ሰግተው አዳራሽ ውስጥ እንዳሉ መንግስትና የዩኒቨርሲቲ አስተዳደሮች ጠንቅቀው እንደሚያውቁ እናምናለን። 

አሁንም ተማሪዎች የሚልኳቸው መልዕክቶች ጉዳዩ ይመለከታቸዋል ለምንላቸው አካላት በሙሉ እየላክን ነው። መረጃው እንዳላቸው ብናውቅም የኛን ኃላፊነት እንወጣለን። አሁንም ችግሮች ይፈቱ፣ ተማሪዎች ያሉበት ሁኔታ በአግባቡ ይፈተሽ፣ መፍትሄ ይፈለግ፣ ከህግ በላይ የሆኑ አካላት ይጠየቁ፣ በዩኒቨርሲቲ ውስጥ ያለው ስርዓት አልበኝነት መፍትሄ ይፈለግለት፣ ዩኒቨርሲቲዎች ከታች እስከ ላይ ይፈተሹ ይመርመሩ እንላለን።

የአንድ ተማሪ ጉዳይ ይመለከተናል!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

Report Page