#ETH

#ETH


"አገራችን ኢትዮዮያ እጅግ አስፈሪና አደገኛ ሁኔታ ላይ ትግኛለች!" - ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል

.

.

አገራችን ኢትዮጵያ፣ እጅግ አስፈሪና አደገኛ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ በዛሬው ዕለት በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ ለሁለተኛ ጊዜ ህገ መንግስትና ህብረ ብሄራዊ ፌደራሊዝም ስርዓትን የማዳን አገር አቀፍ መድረክ ላይ ለመሳተፍ ለመጡ ተሳታፊዎች የመክፈቻ ንግግር ያቀረቡት ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ገለፁ፡፡

ዶ/ር ደብረፅዮን አገራችን ውስጥ ህገ መንግስቱ በግላጭ በሚጣስበት፣ የሰላም እጦትና የዜጎች ደህንነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ በመጣበት፣ መፈናቀልና የንብረት ውድመት የዘወትር ተግባር በሆነበትና የዜጎች ህይወት መጥፋት በተበራከተበት ጊዜ ላይ እንገኛለን ካለ በሗላ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የጠቅላይነት አስተሳሰብ የተጫናችው ተግባራት በአግሪቱ እይተፈፀሙ እንደሚገኙ አብራርተዋል፡፡

ይህን መሰል አደገኛ ተግባራት በሚፈፀሙበት ጊዜ አገራችን ከጥፋት ለማዳን ውይይት ማድረግ ተገቢ ነው የሚሆነው፤ ያሉት ዶ/ር ደብረፅዮን ወይይቱ ለመሳተፍ በዙ ጫናዎች ችለው በመድረኩ ለተገኙ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ሀሳብን የሚፈሩና የሚጠየፉ ፈሪዎች ከነሱ የተለየ ሀሳብ ያላቸው አካላት እዚሁ መድረክ እንዳይገኙ የተለያዩ ጫናዎች ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ በዚሁ ምክንያትም ቁጥራቸው የማይናቅ አካላት ጫናው ከብደዋቸው ከመድረኩ ቀርተዋል፡፡ ይሁንና እነዚህ ሰዎች በሀሳብ እኛ ጋር በመሆናችው እዚሁ መድረክ ባይገኙም በያሉበት ሆነው ትግላቸውን አያቆሙም ያለው ጓድ ደብረፅዮን ሀሳብን ፈርተው የማፈን ስራ ሲሰሩ ለቆዩ ፈሪዎች ግን ወደ ፊት የሰሩትን ዝርዝር ተግባር ወደ ማጋለጥ ተግባር እንደሚገባ፣ የማፈን ተግባሩም እንደማያዋጠና አሸናፊም እንደማይሆን ገልፀዋል፡፡

በመጨረሻም በአሁኑ ሰአት አገራችን ከገጠማት እጅግ አስፈሪና አጣበቂኝ ችግር እንድትወጣ ከተፈለገ በመድረኩ የተገኙ የተለያዩ በህገ መንግስቱና ህብረ ብሄራዊ ፌደራል ስርዓቱ የሚያምኑ ብሄራዊና አገር አቀፍ ፖለቲካዊ ሀይሎች፣ ምሁራን፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎች፣ የሀይማኖት አባቶችና ምን ማድረግ ይሻለናል የሚል እውነተኛ ውይይት በማድረግ የመፍትሄ ሀሳቦች የሚቀመጥበት መድረክ እንደሚሆን ያለው ፅኑ እምነት ገልፀዋል፡፡ በየትኛውም ቦታ የሚገኝ አገሩ ወዳድ ኢትዮያዊም አገራችን ከገጠማት ችግር ለማዳን የበኩሉ እንዲያበረክት ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

ለሁለተኛ ጊዜ ህገ መንግስትና ህብረ ብሄራዊ ፌደራሊዝም ስርዓትን እንታደግ በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ በሚገኘው አገር አቀፍ መድረክ ላይ ተገኝቶ ንግግር ያደረገ የውይይቱ አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ሙሉጌታ በአካሉ በመድርኩ ከ 50 በላይ ብሄራዊና አገር አቀፍ ፖለቲካዊ ፓርቲዎች እንደተገኙ፣ ከ 700 የሚበልጡ ከተላያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ምሁራን፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎችና የሀይማኖት አባቶችና በመድረኩ እየተሳተፉ እንደሆኑ ገልፀዋል፡፡

መድረኩ እስከ ነገ የሚቆይ ሲሆን የህገ መንግስቱና ህብረ ብሄራዊ ፌደራል ስርዓቱ ትሩፋቶና በአሁኑ ሰአት የገጠሙት ተግዳሮቶችና የመፍትሄ ሀሳቦች፣ የህግ የበላይነትና የዜጎች ደህንነት፣ እንዲሁም መሰል ወቅታዊ ጉዳዮችን የሚዳስሱ አምስት ጥናታዊ ፅሁፎች በመድረኩ ቀርበቅው ውይይት እንደሚደረግባቸው ገልፀዋል፡፡

(TPLF)

Report Page