#ETH

#ETH


የገንዘብ ገቢ ማድረግና የውጭ ምንዛሬ መጠቀም የሚያስችል የኤቲኤም አገልግሎት ተጀመረ!

የገንዘብ ገቢ ማድረግና የውጭ ምንዛሬ መመንዘር የሚያስችል የኤቲኤም (ATM) ማሽን በሙከራ ደረጃ የኢትዮጵያ ንግ ባንክ ተግባራዊ ማድረጉን አስታወቀ።

አዲስ የATM የገንዘብ ገቢ ማድረግና የውጭ ምንዛሬ መመንዘር የሚያስችል የATM ማሽን አገልግሎት በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፍንፍኔ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ንጉሴ ለማ አስታውቀዋል።

እንደ አቶ ንጉሴ ገለፃ ቀደም ሲል አገልግሎት ላይ ከዋለው የገንዘብ መክፈያ የATM ማሽን በተጨማሪ አዲሱ ማሽን ወጪ ብቻ ሳይሆን ደንበኞች ገንዘብ ወደ ሂሳባቸው ገቢ ማድረግ እና የውጭ ምንዛሬ ማግኘት የሚችሉበት ነው።

ይህ አገልግሎት ለመጀመርያ ጊዜ በስራ ላይ የዋለው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መሆኑ የጠቆሙት ስራ አስኪያጁ ፤ ማሽኑ በአሁኑ ሰኣት በሙከራ ደረጃ በፍንፍኔ ቅርንጫፍ አገልግሎቱ መጀመሩን ተናግረዋል።

ይህ ማሽን ስራ ከማቀላጠፍና ከማቃለል በተጨማሪ በተለይ ባንኮች ክፍት በማይሆኑበት ዕለታት ደንበኞች የእለተ እለት ስራቸውን ለማቀላጠፍ እንዲችሉ ታሳቢ ተደርጎ እየተዘጋጀ መሆኑን አቶ ንጉሴ ጠቁመዋል።

አጠቃቀሙ በተመለከተ አቶ ንጉሴ ለማ እንዳገለፁት ደንበኞች ካርዱን ወደ ማሽኑ በማስገባትና የሚስጥር ቁጥሩ በመጠቀም የሚመጡት አማራጮች ላይ በተጨማሪ የገንዘብ ማስገባት የሚል በመጫን ገንዘባቸው ወደ ሂሳባቸው ማስገባት ይችላሉ።

(የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia


Report Page