#ETH

#ETH


በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ ፍሬህይወት ቁጥር አንድ ትምህርት ቤት የተፈጠረው ምንድን ነው?

የልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አባወይ ዮሃንስ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ችግሩ የተፈጠረው ዛሬ ረፋድ ላይ በፍሬህይወት ቁጥር አንድ ትምህርት ቤት የ5ኛ እና 7ኛ ክፍል ተማሪዎች ላይ ነው።

በተማሪዎቹ እና መምህራን ላይ የማስታወክ፣ተቅማጥ እና አቅም ማነስ አይነት የጤና እክል ተፈጥሯል። ችግሩ የተፈጠረው አራት ሰዓት ላይ ቁርስ ከተመገቡ በኋላ ቢሆንም የጤና እክሉ የተፈጠረው ምግቡን የበሉትም ያልበሉትም ናቸው ብለዋል።

በመምህራን ላይም የጤና እክል እንደገጠመም ሃላፊው ገልጸዋል። የተፈጠረውን ክስተት ለማወቅ በዘውዲቱ እና ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ምርመራ እየተካሄደ ሲሆን አሁን ላይ የምግብ መመረዝ ተፈጥሯል ማለት አይቻልም ብለዋል።

በተፈጠረው እክል የተጎዱ ተማሪዎች ቁጥርም እስካሁን አልታወቀም ብለዋል ሃላፊው። ችግሩ የታየባቸው ተማሪዎችና መምህራን ወደ ህክምና ተቋም ተወስደው ህክምና እያገኙ ነው ችግሩ የተከሰተውም በሁሉም ተማሪዎች ላይ ባለመሆኑ ወላጆች እንዲረጋጉ ሃላፊው አሳስበዋል።

(ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8)


(Lideta sub city communication affairs office)

በልደታ ክፍለ ከተማ በፍሬ ህይወት ቁ.1 አፀደ ህጻናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በዛሬው ዕለት ተማሪዎች የገጠማቸው ሁኔታ ከምግብ መመረዝ ጋር ግንኙነት እንደሌለው እና ተማሪዎችም በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ገለፀ፡፡

በአንዳንድ ድህረ ገፆችና ሚዲያዎች ችግሩ በክፍለ ከተማው በሦስት ት/ቤቶች እንደተከሰተ ተደርጎ የተገለፀው መረጃ ከእውነት የራቀ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከዚሁ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን እየተከታተልን የምናቀርብ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

(Lideta sub city communication affairs office)

Report Page