#ETH

#ETH


የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣውን ረቂቅ አዋጅ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መራ።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣውን ረቂቅ አዋጅ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መርቷል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላቱ የተለያዩ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን ካነሱ በኋላ ነው ምክር ቤቱ ረቂቁን ለህግ፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር እይታ የመራው።


በተጨማሪም ምክር ቤቱ የፌዴራል የአስተዳደር ስነስርአት ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለዝርዝር እይታ ለህግ፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እንዲሁም በተባባሪነት ለሰው ሃብትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቷል።

የፌዴራል የአስተዳደር ስነስርአት ረቂቅ አዋጁ ሁሉንም የአስተዳደር ተቋማት አቃቤ ህግ መዝግቦ እንዲይዝ የሚደነግግ ነው። ነገር ግን በወንጀል ስነስርአት ህጉ በሚመሩ የአቃቤ ህግና የፖሊስ ተግባራት እንዲሁም በመከላከያና ደህንነት ተቋማት ላይ ተፈፃሚ አይሆንም ተብሏል።

በሃሰተኛ መረጃዎች የተነሳ በሃገሪቱ የሰው ህይወት ሲጠፋ እና ንብረትም ሲወድም የሚስተዋል ነው። በመሆኑም ይህ ረቂቅ አዋጅ የጥላቻ ንግግርና ሃሰተኛ መረጃዎች ስርጭትን በህግ መከልከል አስፈላጊ በመሆኑ ነው የወጣው ተብሏል።

(EBC)


Report Page