#ETH

#ETH


#AddisAbeba

በአዲስ አበባ ከተማ ለአረንጓዴ ቦታነት ተከልለው የነበሩ ቦታዎች ከግሉ ዘርፍ ጋር በጋራ በመሆን ፓርክ እንዲሰራባቸው ተወሰነ፡፡ በከተማዋ በተለያዩ ቦታዎች ለአረንጓዴ ቦታነት በሚል ለረጅም አመታት ተከልልው የነበሩ ቦታዎች ቢኖሩም ለህብረተሰቡ አገልግሎት እየሰጡ እንዳልነበረ የከንቲባ ፅህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም አካባቢዎቹ ለህገወጥ የመሬት ወረራ የተጋለጡ እና ለቆሻሻ ማከማቻነት የዋሉ ሆነዋል፡፡ ይህንን የገመገመው የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔም ቦታዎቹ ከባለሃብቶች ጋር በመሆን የተሟላና ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች ያማከሉ መዝናኛ ያላቸው ፓርኮች እንዲሰራባቸው ወስኗል፡፡

ፓርኮቹ ለነዋሪዎች ተጨማሪ የመዝናኛ አማራጭ እንደሚሆኑና የከተማዋ አረንጓዴ ሽፋን ለማሳደግም የካቢኔው ውሳኔ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ በከተማዋ የሚገኙ የህዝብ መዝናኛ ማእከሎችን ማሳደግ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝም ነው ፅህፈት ቤቱ ያስታወቀው፡፡

(Mayor Office AA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia


Report Page