#ETH

#ETH


የፓራዳይዝ ቫሊ ኮሌጅ አዳማ ካምፓስን ሙሉ ለሙሉ መዝጋቱን ኤጀንሲው ገለጸ!

በፈጸሙት መመሪያ ጥሰቶች ምክንያት ህዳር 9 ቀን 2012 ዓ.ም ኤጀንሲው ውሳኔ ካስተላለፈባቸው ሁለት የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ አንዱ ለፓራዳይዝ ቫሊ ኮሌጅ አዳማ ካምፓስ ነው፤ ኮሌጁ በአውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂና አውቶሞቲቭ ኢንጂነሪንግ የትምህርት መስኮች የእውቅና ፈቃድ ሳይሰጠው ተማሪ ተቀብሎ እያስተማረ መሆኑ ስለተረጋገጠ በፕሮግራሞቹ ለ2 ዓመት የእወቅና ፈቃድ እንዳይሰጠው ጥቅምት 28 ቀን 2012 ዓ.ም. ለኮሌጁ ማሳወቁን አስታውሷል፡፡ ሆኖም ግን አሁንም በዚሁ አዳማ ካምፓስ በፋርማሲ የትምህርት መስክ የእውቅና ፈቃድ ሳይኖራችሁ ተማሪ በመቀበል እያስተማራችሁ መሆናችሁን ለማረጋገጥ ችለናል፡፡

ተደጋጋሚ በተፈጸሙ ጥፋቶች ምክንያት ስለሆነም የተፈጸመው ጥፋት የከፍተኛ ትምህርት አዋጅንና የከፍተኛ ትምህርት የስነ ስርዓት መመሪያ የጣሰ ስለሆነ ፓራዳይዝ ቫሊ አዳማ ካምፓስ ከህዳር 09 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ሙሉ በሙሉ የተዘጋ መሆኑን በመግለጽ፣ የእውቅና ፈቃድ ያልተሰጣቸውን ሶስቱን ማለትም የአውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ፣ አውቶሞቲቭ ኢንጂነሪንግ እና ፋርማሲን ሳይጨምር በመመማር ላይ ያሉ የተማሪዎችን ዝውውር ለመፈጸም ያመች ዘንድ በካምፓሱ እውቅና ፈቃድ በተሰጣችሁ የትምህርት መስኮች እየተማሩ ያሉ ህጋዊ ተማሪዎችን ስም ዝርዝር እስከ ህዳር 17 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ለኤጀንሲው ሪፖርት እንዲያደርግ ውሳኔ ተላልፏል፡፡

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የእውቅና ፈቃድ ያልተሰጠባቸውን ማለትም የአውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ፣ አውቶሞቲቭ ኢንጂነሪንግ እና ፋርማሲን ሳይጨምር የእውቅና ፈቃድ በተሰጠባቸው የትምህርት መስኮች ብቻ ተመዝግበው በመማር ላይ የነበሩ ተማሪዎች በአዳማ ከተማ እውቅና ፈቃድ ካላቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚፈልጉትን መርጠው ለኤጀንሲው እንዲያሳውቁ ኤጀንሲው አሳስቧል፡፡

-------------- -------------- --------------

(ለኮሌጁ የተላለፈው ዝርዝር ውሳኔን በሚመለከት ከዚህ በታች ያንብቡ)

ለፓራዳይዝ ቫሊ ኮሌጅ (አዳማ ካምፓስ)

አዳማ፣

ጉዳይ፡- ለተፈጸመ የመመሪያ ጥሰት የተላለፈውን ውሳኔ ስለማሳወቅ

ኮሌጃችሁ በአዳማ ካምፓሱ የዕውቅና ፈቃድ ባልተሰጠባቸው በአውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂና አውቶሞቲቭ ኢንጂነሪንግ የትምህርት መስኮች ተማሪዎችን መዝግቦ በማስተማሩ በቁጥር 01/ገ-1/1937/12 በቀን 28/02/2012 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ በኘሮግራሞቹ ለ2 ዓመት እውቅና እንደማይሰጣችሁ እና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ መስጠታችን ይታወቃል፡፡

ሆኖም ግን አሁንም በዚሁ አዳማ ካምፓስ በፋርማሲ የትምህርት መስክ የእውቅና ፈቃድ ሳይኖራችሁ ተማሪ በመቀበል እያስተማራችሁ መሆናችሁን ለማረጋገጥ ችለናል፡፡ ስለሆነም የፈጸማችሁት ጥፋት የከፍተኛ ትምህርት አዋጅንና የከፍተኛ ትምህርት የስነ ስርዓት መመሪያ የጣሰ ስለሆነ ፓራዳይዝ ቫሊ አዳማ ካምፓስ ከዛሬ ከህዳር 09 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ሙሉ በሙሉ የተዘጋ መሆኑን እየገለጽን፣ የተማሪዎችን ዝውውር ለመፈጸም ያመች ዘንድ በካምፓሱ እውቅና ፈቃድ በተሰጣችሁ የትምህርት መስኮች እየተማሩ ያሉ ህጋዊ ተማሪዎችን ስም ዝርዝር እስከ ህዳር 17 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ለኤጀንሲው ሪፖርት እንድታደርጉ እናስታውቃለን፡፡

ከሠላምታ ጋር

ግልባጭ፣

• ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ጽ/ቤት


Report Page