#ETH

#ETH


ለኢትዮ ስማርት ኮሌጅ ተሰጥቶት የነበረውን የድህረ-ምረቃ እውቅና ፈቃድ መሰረዙን ኤጀንሲው ገለጸ!

በፈጸሙት መመሪያ ጥሰቶች ኤጀንሲው ውሳኔ ካስተላለፈባቸው የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም አንዱ ኢትዮ ስማርት ኮሌጅ ነው፤ ኤጀንሲው ተቋሙ የፈጸመውን የህግ ጥሰት በመመርመር ለኮሌጁ ተሰጥቶት የነበረውን የድህረ ምረቃ የእውቅና ፈቃድ ከህዳር 9 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ የተሰረዘ መሆኑን በመግለጽ የተመዘገቡና በመማር ላይ ያሉ ተማሪዎች ካሉት ዕውቅና ወዳላቸው ተቋማት ለማዛወር ያመች ዘንድ ዝርዝራቸውን እስከ ህዳር 19 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ለኤጀንሲው ሪፖርት እንዲቀርብ ህዳር 9 ቀን 2012 ዓ.ም ለኮሌጁ በጻፈው ደብዳቤ አሳውቋል፡፡

(ለኮሌጁ የተላለፈው ዝርዝር ውሳኔን በሚመለከት ከዚህ በታች ያንብቡ)

ለኢትዮ ስማርት ኮሌጅ

አድዋ፣

ጉዳዩ፡- ለተፈጸመ የመመሪያ ጥሰት የተላለፈውን ውሳኔ ስለማሳወቅ

ኮሌጃችሁ በቀን 27/01/2012 በቁጥር 01/7-1/4166/12 በተፃፈ ሰርተፊኬት በማስተር ኦፍ ቢዝነስ አድሚንስትሬሽን እና በማስተር ኦፍ ሳይንስ ኢን አካውንቲንግ ኤንድ ፋይናንስ የእውቅና ፈቃድ መስጠቱ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን ኮሌጃችሁ እውቅና ፈቃድ ከተሰጠው አግባብ ውጭ፡-

1. በማስተር ኦፍ ቢዝነስ አድሚንስትሬሽን የተሰጠውን የእውቅና ፈቃድ ተቋማችሁ በ7 የMBA ዘርፎች የእውቅና ፈቃድ እንደተሰጣችሁ በማስመሰል እና

2. በየአመቱ ለእያንዳንዱ የትምህርት መስክ ከ40 ያልበለጡ ተማሪዎች መቀበል እንደምትችሉ ቢገለጽላችሁም ኤጀንሲው የሰጠውን ሠርተፈኬት እንደገና በመከለስና በማስተካከል በየዓመቱ በእየአንዳንዱ የትምህርት መስክ 250 ተማሪዎችን የመቀበል ፈቃድ እንደተሰጣችሁ አስመስላችሁ በማስተዋወቅ ለማህበረሰቡ የተሳሳተ መረጃ ስታስተላልፉ ተገኝታችኋል፣

3. በኮምፒውተር ኢንጂነሪንግ የዕውቅና ፈቃድ ሳይኖራችሁ ተማሪዎችን ተቀብላችሁ በማስተማር ላይ እንደምትገኙ ለማወቅ ተችሏል፣

ስለሆነም ኤጀንሲው ተቋሙ የፈጸመውን የህግ ጥሰት በመመርመር በድህረ ምረቃ የተሰጣችሁ የእውቅና ፈቃድ ከህዳር 9 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ የተሰረዘ መሆኑን እየገለጽን የተመዘገቡና በመማር ላይ ያሉ ተማሪዎች ካሉ ዕውቅና ወዳላቸው ተቋማት ለማዛወር ያመች ዘንድ ዝርዝራቸውን እስከ ህዳር 19 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ለኤጀንሲው ሪፖርት እንድታደርጉ እናስታውቃለን፡፡

ከሠላምታ ጋር

ግልባጭ፣

• ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ጽ/ቤት

• ለኢፌዲሪ ጠቅላይ አቃቤ ህግ

• ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታዎች ጽ/ቤት

• ለግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማህበር ጽ/ቤት

አዲስ አበባ፣

• ለትግራይ ብ/ክ/መ/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት

• ለትግራይ ብዙሃን መገናኛ ኤጀንሲ

ትግራይ፣

• ለአድዋ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት

አድዋ፣

• ለዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት

• ለም/ዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት

• ለዕው አሰጣጥ ዳይሬክቶሬት

• ለህግ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

• ለኮሚኒዩኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

ከትአጥኤ


Report Page