#ETH

#ETH


በነገው እለት በሚካሄደው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ምክንያት ከንጋቱ 11 ሰአት ጀምሮ ውድድሩ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚደረጉ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ይፋ አደረገ።

በርካታ ህዝብ የሚሳተፍበት ታላቁ ሩጫ መነሻውና መድረሻውን መስቀል አደባባይ በማድረግ በነገው እለት ማለትም ህዳር 7 ቀን 2012 ዓ.ም ይካሄዳል።

በዚህም መሰረት በርካታ ህዝብ የሚሳተፍበት የጎዳና ሩጫው ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ፡-

• ከአፍሪካ ህብረት አደባባይ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ

• ለልደታ ፀበል ወደ ልደታ ብሪሞ ሜዳ

• ከልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወደ ሜክሲኮ

• ከአብነት በጆሳንሰን ወደ 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ

• ከሞላ ማሩ ወደ ጨፌ ሜዳ

• ከበርበሬ በረንዳ ወደ 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ

• ከተክለሃይማኖት ወደ ጥቁር አንበሳ

• ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ ብሔራዊ ቲያትር

• ከንግድ ማተሚያ ቤት ወደ አምባሳደር ቲያትር ፍልውሃ

• ከገብርኤል መሳለሚያ ወደ መስቀል አደባባይ

• ከገብርኤል መሳለሚያ ወደ ካሳንቺስ

• ከአዋሬ ሴቶች አደባባይ ወደ ካሳንቺስ ቶታል

• ከዘሪሁን ህንፃ ወደ ኡራኤል

• ከአትላስ መብራት ወደ ኡራኤል

• ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል አደባባይ

• ከኦሎምፒያ ባምቢስ ኡራኤል

• ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ

• ከጨርቆስ አዲሱ መንገድ ወደ ለገሃር መብራት

• ከቡልጋርያ ወደ ገነት መብራት ሜክሲኮ አደባባይ

• ከጠማማ ፎቅ በንግድ ምክር ቤት ሜክሲኮ አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ከንጋቱ 11 ሰአት ጀምሮ ውድድሩ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚደረጉ ተገልጿል።

ስለሆነም አሽከርካሪዎች ሌሎች አመራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ እና ከህዳር 6 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ በተጠቁስት መስመሮች ግራና ቀኝ ለረዥም ሆነ ለአጭር ሰዓት ተሸከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን አሽከርካሪዎች ተገንዝበው ትብብር እንዲያደርጉ ኮሚሽኑ አስታውቋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አክሎም ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የሚያዘጋጀው የጎዳና ላይ ሩጫ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ የፀጥታ አካለት ዝግጅታቸውን አጠናቀው ወደ ስራ መግባቱን አስታውቋል።

ውድድሩ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ከተለያዩ አካላት የተውጣጣ የፀጥታ ኮሚቴ ታዋቅሮ እቅድ በማውጣት እና ሩጫውን በበላይነት ከሚመራው ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ኃላፊዎች ጋር በመወያየት ወደ ተግባር መግባቱን ኮሚሽኑ ገልጿል።

ከዚህ ቀደም የተካሄዱት ተመሳሳይ የጎዳና ላይ ሩጫዎች በሰላም መጠናቀቃቸውን ኮሚሽኑ አስታውሶ ሩጫው የሀገርን መልካም ገፅታ ለመገንባት የራሱ ጠቀሜታ ስለሚኖረው የዘንድሮ ውድድር ስኬታማ ሆኖ በሳለም እንዲጠናቅ የውድድሩ ተካፋዮች ሆኑ መላው ነዋሪው እንደ ከዚህ ቀደሙ ከፀጥታ ኃይሉ ጎን በመቆም አስፈላጊው ትብብር እንዲያደርግ ኮሚሽኑ ጥሪውን አቅርቧል።

በውድድሩ ላይ የህዝብን ሰላምና ደህንነት የሚያውኩ ያልተገቡ መልእክቶችን ማስተላለፍ ይሁን ሌሎች ህገ ወጥ እንቀስቃሴዎችን ማድረግ የህግ ተጠየቂነትን የሚስከትል ስለሆነ ተሳታፊዎች ይህንን ተገንዝበው ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደለባቸውም አሳስቧል።

በመጨረሻም ህብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ሆነ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት መረጃ ለመስጠት 991 ወይም 816 ነፃ የስልክ መስመሮችን እና 01- 11 -11- 01 -11፣ 01- 11- 26- 43- 59፣ 01- 11- 01- 02- 97፣ መጠቀም እንደሚቻል ተገልጿል።

(FBC)

Report Page