#ETH

#ETH


በወለጋ ዩኒቨርሲቲ ጊምቢ "ካምፓስ" ላይ ትናንት ሕዳር 4/2012 ዓ.ም መጠነኛ ችግር ተፈጥሮ የተወሰኑ ተማሪዎች ቀላል ጉዳት እንደደረሰባቸው ስለሁኔታው መረጃ ያደረሱን ተማሪዎች ተናግረዋል። የመከላከያ ሠራዊት በመግባቱ ችግሩ ቢበርድም ስጋት ላይ በመሆናቸው በየዶርሙ ተሰባስበው መቀመጣቸውንም ተማሪዎች ተናግረዋል፡፡

በወለጋ ዩኒቨርሲቲ የጊምቢ "ካምፓስ" ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዳይሬክተር ቀናቴ ነጋሳ እንደተናገሩትም ትናንት ጠዋት በተማሪዎች መመገቢያ አካባቢ ተማሪዎች ድንጋይ በመወራወራቸው የተወሰኑ ችግሮች ቢፈጠሩም ችግሩን በፀጥታ ኃይሉ መቆጣጠር ተችሏል፡፡ ተማሪዎቹ ሠላም አውርደው ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ በሀገር ሽማግሌዎች፣ በሃይማኖት አባቶች፣ በአባገዳዎች እና በዩኒቨርሲቲው ጥረት እየተደረገ እንደሆነም ነግረውናል፡፡ ጉዳት እንዳይደርስ ጥንቃቄ እያደረጉ መሆኑንም ነው ያረጋገጡልን፡፡

(AMMA)

Report Page