ETH

ETH

ቲክቫህ ኢትዮጲያ

ኢትዮ ቴሌኮም ከቴሌግራም፣ ዋትስ አፕ እና መሰል ኩባንያዎች የሚገባውን ጥቅም ለማግኘት ጥናት መጀመሩን አስታወቀ።

እንደ ቫይበር፣ ዋትስ አፕ፣ ቴሌግራም ያሉ እና ሌሎችም የስልክ መተግበሪያዎች ያሏቸው ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ደርምሰውን ገብተው ለህብረተሰቡ አገልግሎት እየሰጡ ቢገኙም የሚያገኙትን ጥቅም ለማጋራት የሚያስችል አሰራር እንደሌለው ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ማርኬቲንግ ሀላፊ አቶ ኤፍሬም አረፋአይኔ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ደንበኞቻችን አነዚህን የስልክ መተግበሪያዎች ለመጠቀም ኢንተርኔት ያስፈልጋቸዋል ለዚህ ደግሞ ክፍያ ይከፍላሉ በዚያ ኢትዮ ቴሌኮም ይጠቀማል ብለዋል፡፡

ይሁንና ኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞችን ከማስከፈል ባለፈ ከኩባንያዎቹ ላይ ጥቅም መጋራት የሚስችል ስርዓት አስካሁን ለምን አልዘረጋም? ስንል ጠይቀናል፡፡

አቶ ኤፍሬምም ይህን ለማድረግ ኩባንያዎቹን ከማነጋገር ጀምሮ በርካታ ቴክኒካል የሆኑ ቅድመ ዝግጅቶችን ማድረግ ስለሚያፈልግ ነው ብለውናል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም ይህንን ስርዓት ባለመዘርጋቱ ምን ያህል ገንዘብ ያጣል ብለን ብንጠይቅም በዚህ ደረጃ ተጠንቶ የተቀመጠ መረጃ እንደሌለ ከሀላፊው ሰምተናል፡፡

በድርድርም ሆነ በቴክኖሎጂ ከእነሱ በመብለጥ ገቢ መካፈል ተገቢ በመሆኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው አሰራር ምን ይመስላል የሚለው እየተጠና መሆኑንም ሰምተናል፡፡

የተለያዩ አገራት ፌስቡክ፣ጎግል፣ዋትስ አፕ፣ ትዊተርና መሰል ኩባንያዎች እና ተጠቃሚዎች ላይ ተጨማሪ ታክስ የመጫን ፍላጎት በማሳየት ላይ ናቸው።

ፈረንሳይ ባሳለፍነው ዓመት በአሜሪካ ግዙፍ ከባንያዎች ላይ በተለይም ጎግልና ፌስቡክ ላይ የ3 በመቶ ታክስ መጣል የሚያስችላትን ህግ ያዘጋጀት ሲሆን እንግሊዝ፣ስፔን፣አውስትራሊያና ጣልያን የፈረንሳይን ፈለግ ለመከተል በሂደት ላይ ናቸው።

የላቲን አሜሪካ እና እስያ አገራት ደግሞ ተመሳሳይ እርምጃዎችን ለመከተል ፍላጎት እንዳላቸው በየጊዜው በመግለጽ ላይ ናቸው።

ዩጋንዳ፣ቤኒን እና ዛምቢያ እነዚህን ኩባንያዎች ትተው በማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ ዜጎቻቸው ላይ ተጨማሪ ታክስ የጣሉ አገራት ናቸው።

በትግስት ዘላለም

Report Page