#ETH

#ETH


"በዩኒቨርሲቲዎቹ ውስጥ ችግር እየፈጠሩ ያሉት ተማሪዎቹ ሳይሆኑ የተማሪዎችን መታወቂያ በመቀማትና ህገወጥ የተማሪዎች መታወቂያ በማዘጋጀት ወደ ግቢው ውስጥ የሚገቡ ግለሰቦች ናቸው!" ዶ/ር ሳሙኤል

ሰሞኑን በአንድ አንድ ዩኒቨርሲቲዎች የተከሰተውን የሰላም መደፍረስ ወደነበረበት ለመመለስና የመማር ማስተማር ስራውን ለማስቀጠል የፌዴራልና የክልል የጸጥታ ሃይሎች የተጠናከረ ስራ በመስራት ላይ መሆናቸውን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት አስታወቀ።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታው ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ በመቱ፣ መዳወላቡ፣ ጅማ እና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲዎች የተፈጠረውን ችግር ለማስወገድ ተማሪዎች፣ በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ፣ በአገር ሽማግሌዎች፣ በሃይማኖት አባቶች ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

ተማሪዎቹ አደጋ ይደርስብናል መማር አልቻልንም አልተረጋጋንም አስተማማኝ ጥበቃ የለንም የሚል ስጋት እንዳላቸው የጠቆሙት ሚኒስቴር ዴኤታው፤ ይህንነ ስጋት ለመቅረፍ ከሚደረገው ውይይት በተጓዳኝ የክልልና የፌዴራል የጸጥታ አካላት የተቀናጀ ስራ እያከናወኑ መሆናቸውንን ችግሩ ከመንግስት አቅም በላይ እንዳልሆነ አስታውቀዋል።

በዩኒቨርሲቲዎቹ ውስጥ ችግር እየፈጠሩ ያሉት ተማሪዎቹ ሳይሆኑ የተማሪዎችን መታወቂያ በመቀማትና ህገወጥ የተማሪዎች መታወቂያ በማዘጋጀት ወደ ግቢው ውስጥ የሚገቡ ግለሰቦች ናቸው ያሉት ዶ/ር ሳሙኤል፤ እነዚህ ግለሰቦች ተማሪዎቹ ምግብ እንዳይበሉ፣ ወደክፍል እንዳይገቡ፣ ከጸጥታ አካላት ጋር እንዲጋጩ የመቀስቀስ ስራ እንደሚያከናውኑ ነው የተናገሩት።

ይህም ሆኖ ችግሩ ከመንግስት ቁጥጥር ውጭ እንዳልሆነ የተቆሙት ሚኒስቴር ዴኤታው ተማሪዎቹ ወደ ትምህርት ገበታቸው በቅርቡ እንደሚመለሱ ተናግረዋል፡፡ አጥፊዎቹም በቁጥጥር ስር እየዋሉ እንደሆነም ተናግረዋል።


(EPA)

Report Page