#ETH

#ETH


በቀን 28/02/2012ዓ.ም ጥዋት 11 ሰአት ላይ በኮምቦልቻ መንበረ ሕይወት መድሐኒዓለም ቤተ ክርስትያን በደረሰው የእሳት ቃጠሎ ከደብሩ ዋና አስተዳዳሪ መላከ ሰላም አባ ሳሙኤል ለሚዲያ አካላት የተሰጠ መግለጫ

ትናንት በ27/02/2012ዓ.ም በመላው ቤተ ክርስያን የሚከበረው የታላቁ በአላችን መድሀኒዓለም የሰው ልጆችን ያዳነበት ነው፡፡ ይህን አስመለክቶ በሺዎች የሚቆጠሩ ምእመናን በተገኙበት በደማቅ ስነስርአት ተከበሯል፡፡ በተጨማሪም በሀገሪቱ ላይ ባለው አለመረጋጋትና መከራ ስደትና የቤተክርስትያን ቃጠሎ አስመልከቶ ቅዱስ ሲኖዶስ በሰጠው መመርያ መሰረት አጠቃላይ በኢትዮጵያ የሚገኙ ገዳማትና አድባራት አምላካችን የመጣውን መከራ እንዲያስታግስልንና ቀጣይ ደግሞ ምእመናኑ ህወታቸውን እንዲጠብቁ ጸሎተ ምህላ ከጀመርን እነሆ ዛሬ አምስተኛ ቀናችን ነው፡፡

የማታው መርሀ ግብር ከንግሱ በአል በላይ የምእመኑ ቁጥር ብዙ ነበር፡፡ በአሉ ፖሊሶችና የፀጥታ አካላት ባሉበት ከቀኑ 11 ሰአት የጀመረው ከምሽቱ 2 ሰአት በሰላም ተጠናቋል፡፡ተረኛ የቤተክርስትያን አገልጋዮች ቁልፉን ለተረኛ ጥበቃ አስረክበው ወጥተዋል፡፡

ሌሊት ተረኛ ካህናት ኪዳን ለማድረስ ወደ ቤተክርስትን ሲሄዱ እሳቱን ሲያዩ በሰአቱ የውስጠኛው ክፍል እየነደደ ነበር፡፡ኡኡታ ተፈጠረ ጥበቃው ጥይት ወደ ሰማይ በመተኮስ የድረሱልን ጥሪ በማቅረብ ሁላችን ጩከት አሰማን

ምእመናኑና ካህናቱ በፖሊስና በጸጥታ አካላት ርብርብ በጌታ ረዳትነት ቤተክርስትያኑ ሊተርፍ ችሏል፡፡ቤተክርስትያኑ ቢተርፍም ከ2 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያለው ከታቦታቱ በቀር መስቀሉ፣ መፅሀፍቱ፣ መንበሩ፣ የወርቅ ወንጌላቱ ሙሉ በሙሉ ወድመዋል፡፡

ቃጠሎው የተነሳው ከቅኔ ማህሌቱ ሳይሆን ከመቅደሱ ውስጥ ነው፡፡ ማን አስነሳው እንዴት ተነሳ ሻማ አብርቶ የወጣው ዲያቆኑ ነው ወይስ ቄሰ ገበዙ ለምን ሳያጠፉ ወጡ የሚለው ከፖሊስ ምርመራ በኋላ አብረን የምናየው ይሆናል፡፡

የኮምቦልቻ ህዝበ ክርሰትያን፣ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣ ወጣቶች፣ ልዩ ሀይሎች፣ ፖሊሶች፣ የጸጥታ አካላት፤የእሳት አደጋ ሰራተኞች ያደረጉት መረባረብ በቤተክርስትያን ስም አመሰግናለው፡፡

በአካባቢው የነበሩ የሙስሊም ማህበረሰቦች ከኛ ጋር አብረው እየጮሁ፣ እየተጨነቁ፣ አፈርና ውሀ እየተሸከሙ እሳቱን ለማጥፋት ያደረጉት ርብርብ መድሀኒዓለም ጤና እና እድሜ ይስጥልን ብለዋል፡፡ ራማ ኮንሰትራክሽን እና ሌሎች ተቋማትና ግለሰቦች ለቤተክረስትኑ ማሰርያ ገንዘብ ያዋጡ ሲሆን የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ለቤተክርሰትያኑ ድጋፍ 50 ሺህ ብር ድጋፍ አድረጓል በማለት መላከ ምህረት ቆሞስ አባ ሳሙኤል ለህዝብና ሚዲያ ግንኑነትና ለአማራ መገናኛ ብዙሀን መግለጫ ሰተዋል፡፡


Report Page