#ETH

#ETH


ለወላይታ ኢንዱስትሪ አብዮት ማስፈጸሚያ የሚሆን ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ተደረገ፡፡

በመደመር ዕሳቤ ለ3 ቀናት ሲሰለጥኑ የቆዩ ከ1360 በላይ አጠቃላይ የወላይታ ዞን አመራሮች ለተጀመረው የኢንዱስትሪ አብዮት ንቅናቄ የሚሆን የ1 ወር ደመወዝ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል፡፡

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኩምቤ እንደገለጹት ለረዥም ጊዜ ከህብረተሰቡ ሲነሳ የቆየው የኢንዱስትሪ ፓርክ ጥያቄ ከሚመለከተው አካል እስካሁን ድረስ ምላሸ ያላገኘ ቢሆንም የህዝቡን የመልማት ጥያቄ ለመመለስ የዞኑ አስተዳደር ከመስከረም 2012 ዓ.ም ጀምሮ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡

የወላይታ እንዱስትሪ አብዮት ለማስፈጸም የሚፈለገው 6 መቶ ሚሊዮን ሲሆን 136 ሚሊየን ብር ባለፈው መስከረም ከተለያዩ የመንግስት መዋቅሮች ቃል የተገባ መሆኑን የጠቀሙት አቶ ዳጋቶ ገቢ የማሰባሰብ ተግባሩ በየደረጃው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

በቁጥር 1360 የሚሆኑ በየደረጃው የሚገኙ አጠቃላይ የወላይታ ዞን አመራሮች ለተግባሩ ማሳኪያ እንዲሆን የ1 ወር ደመወዝ ድጋፍ ለማድረግ ቃል በመግባታቸው አቶ ዳጋቶ አመስግነዋል ፡፡

በዚህ ተግባር በሁሉም መዋቅሮች የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞችን፣የነገዴ ማህበረሰብን፣አርሶ አደሮችን ፣የዲያስፖራ አባላትንና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለማሳተፍ መታቀዱን ዋና አስተዳዳሪው ተናግረዋል፡፡

ከኢትዮጵያ ቴለኮሚንኬሽን ኮርፖሬሽን ጋር በመተባበር ለኢንዱስትሪ ልማቱ ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ለማካሄድ መታቀዱንም አቶ ዳጋቶ አክለዋል፡፡

የቤት ክዳን ቆርቆሮ፣የብረታብረት፣የችፑድና ሌሎችንም ለማምረት በወላይታ የኢንዱስትሪ እንጂኔርንግ ማዕከል ግንባታ በወላይታ ልማት ማህበር በኩል እየተገነባ መሆኑንና ለተለያዩ ማሽኔሪዎች ግዥ ትዕዛዝ መደረጉን አቶ ዳጋቶ ገልጸዋል፡፡

ከተሳታፊ አመራሮች መካከል አንዳንዶቹ ለወላይታ ኢንዱስትሪ አብዮት የ1 ወር ደመወዝ ድጋፍ ለማድረግ በመፍቀዳቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡

ዞኑ ከፍተኛ የሆነ የስራ አጥ ቁጥር ያለበት አካባቢ በመሆኑ ኢንዱስትሪ በመገንባት ችግሩን ለመቅረፍ ለተያዙ ስራዎች ሁሉ በባለቤትነት ስሜት እንደሚሰለፉ አክለዋል፡፡

በሁሉም መዋቅሮች ህብረተሰቡን በማስተባበር ዕቅዱን ለማሳካት ህዝቡ በስፋት እንዲሳተፍ ለማድረግ መዘጋጀታቸውንም አስተያየት ሰጪዎቹ ተናግረዋል፡፡

ዘገባው የወላይታ ዞን የህዝብ ግንኙነት ጽ/ቤት ነው፡፡

Report Page