#ETH

#ETH


ከባድ የመግደል ሙከራ ያደረገዉ ተከሳሽ በፅኑ እስራት ተቀጣ!

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 27(1) እና 539(1)(ሀ) ስር የተመለከቱትን ድንጋጌዎች በመተላለፍ በፈፀመዉ ከባድ የሰዉ ግድያ ሙከራ ወንጀል ክስ ተመስርቶበት የክስ ሂደቱ ሲካሄድ ቆይቷል፡፡

የወንጀል ዝርዝሩ እንደሚያስረዳዉ ተከሳሹ ሰዉን ለመግደል በማሰብ በቀን 27/10/2010 ዓ.ም በግምት ከሌሊቱ 7፡00 ሲሆን በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ክልል ዉስጥ ዘሚካኤል ይርጋሸዋ የተባለን የግል ተበዳይ ጭካኔን በተሞላበት ሁኔታ በመጥረቢያ 1 ጊዜ ጭንቅላቱን፣1ጊዜ ግንባሩንና በመጥረቢያዉ እጀታ እግሩን በመምታት የራስቅል አጥንት ስብራትና የአጥንት መሰርጎድ እንዲደርስበት አድርጓል፡፡

በተጨማሪም በግል ተበዳይ ላይ በጭንቅላቱ ና በግንባሩ ላይ መፈንከት እንዲደርስበት፣ የቀኝ እግሩ ላይ ቅጥቅጥና በግራ ታፋ እና ጉልበቱ ላይ የእብጠት ጉዳት እንዲደርስበት ያደረገ በመሆኑ በፈፀመዉ ከባድ የመግደል ሙከራ ወንጀል በዐቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶበታል፡፡

ክሱን የመሰረተዉ በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ልደታ ምድብ ፅ/ቤት ዐቃቤ ህግም 3 የሰዉ፣ከቅዱስ ጳዉሎስና ከቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል የመጡ 2 የህክምና የሰነድ ማስረጃዎችንና የገላጭ ዝርዝር ማስረጃዎቹን አያይዞ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል፡፡

የክስ ሂደቱን የተከታተለዉ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የወንጀል ችሎትም የቀረቡትን ማስረጃዎች ከመረመረ በኋላ ተከሳሽ በወንጀል ድንጋጌ ደረጃ 1 እርከን 38 ስር ጥፋተኛ ነዉ ሲል ወስኗል፡፡ በዚሁ መሰረት በተከሳሽ ላይ የቀረበ የቅጣት ማክበጃ ባለመኖሩና ከዚህ በፊት ሪከርድ የሌለበት መሆኑ በማቅለያነት ይዞለት በእርከን 37 ስር በቀን 19/02/12 በዋለዉ 20ኛ የወንጀል ችሎት ተከሳሽ በሌለበት በ10 አመት ፅኑ እስራት ይቀጣ ወስኖበታል፡፡

Report Page