#ETH

#ETH


የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ4ኛው የወንጀል ችሎት በአበርገሌ ወረዳ በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩትን ከፍተኛ አመራሮች በዋስ እንዲለቀቁ ወስኗል።

የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ4ኛው የወንጀል ችሎት በአበርገሌ ወረዳ በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩት ከፍተኛ አመራሮች በዋስ እንዲለቀቁ ወሰነ።

ፍርድ ቤቱ ተጠርጣሪዎቹ በዋስ እንዲፈቱ የወሰነው መርማሪ ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀን ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ወድቅ በማድረግ ነው።

መርማሪ ፖሊስ ከኢትዮ ቴሌኮም የስልክ ልውውጥ መረጃ በቴክኒክ ችግር ምክንያት አልደረሰልኝም የሚልና በወረዳው የአራት ተቋማት የኦዲት ምርመራ ውጤት አለመድረሱን በመጥቀስ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ጠይቆ ነበር።

ተጠርጣሪዎችም የእጅ ስልካቸውን ከሰጡ ከ30 ቀናት በላይ መሆኑንና ኦዲት የሚደረጉ ተቋማትም በዋና እና ምክትል ሃላፊ የሚመሩ በመሆናቸው የዋስትና መብት እንደማያስከለክል ጠቅሰው ተከራክረዋል።

ችሎቱ ግራ ቀኙን ከመረመረ በኋላ ተጠርጣሪዎች በዋስ ቢወጡ በኦዲት ስራውም ሆነ የስልክ ቅብብሎሹን ለማጣራት የሚያሳድሩት ተጽእኖ ሊኖር አይችልም በማለት በ15 ሺህ ብር ዋስትና እንዲለቀቁ ወስኗል።

የዋስትና መብት የተሰጣቸውም የአበርገሌ ወረዳው ዋና አስተዳዳሪ፣ የአዴፓ ጽህፈት ቤት ኃላፊ፣ በአዴፓ ጽህፈት ቤት የህዝብ ግንኙነት አደረጃጀትና የሚሊሻ ጽህፈት ቤት ሃላፊ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ከመስከረም 25/2012 ዓ.ም ጀምሮ በእስር ላይ ሆነው ጉዳያቸውን ሲከታተሉ መቆየታቸው የሚታወስ ነው፡፡

(ENA)

Report Page