#ETH

#ETH


በመኖሪያ በቱ ብሬን (የመትረየስ ጠመንጃ) የሆነ የቡድን የጦር መሳሪያ ከመሰል 83 ጥይት እና 30 የሽጉጥ ጥይቶችን ሸሽጎ ለመሸጥ ሲያስማማ የነበረ ግለሰብ ተይዞ ምርመራ እያጠራ መሆኑን የአበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ!

ግለሰቡ እና የጦር መሳሪያው ሊያዝ የቻለው ከህብረተሰቡ የተገኘን መረጃ መነሻ በማድረግ ነው፡፡ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ቦታው ኮተቤ መሳለሚያ ተብሎ ከሚጠራው ስፍራ አንድ ግለሰብ በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ አንድ ብሬን (የመትረየስ ጠመንጃ) የቡድን የጦር መሳሪያ ከመሰል 83 ጥይቶች እና ከ30 የሽጉጥ ጥይቶች ጋር ደብቆ ገዥ በማፈላለግ ላይ እንዳለ መረጃ የደረሰው የፌዴራልና የአበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከሕብረተሰቡ ያገኘውን መረጃ መሰረት በማድረግ በተደረገው ብርቱ ክትትል ሁኔታውን ለቅርብ ኃላፊዎቻቸው አሳውቀው ለፖሊስ በቂ ማስረጃ በማሰባሰብ ግለሰቡ የጦር መሳሪያውን አሳልፎ ሳይ ሸጠው ከፍ/ቤት የመበርበሪያ ትዕዛዝ በማውጣት በመኖሪያ ቤቱ ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ የጦር መሳሪያውንና ጥይቶቹን ማግኘቱን የጉዳዩ መርማሪ ም/ሳጅን ጌታነህ ታረቀኝ ገልፀዋል፡፡

ተጠርጣሪው መሳሪያውን ለመሸጥ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ሲያደርግ እንደነበረ የምረመራ መዝገቡን ዋቢ በማድረግ የገለፀው መርማሪ ጉዳዩ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የካ ምድብ ችሎት እየታየ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ መርማሪው ባአስተላለፉት መልዕክት የጦር መሳሪያ መሸጥ፤ማዛዋወርና አሳልፎ መስጠት ፈፅሞ ህገወጥ ተግባር ከመሆኑ ባሻገር ለከተማችን ሰላም መታወክ ምክንያት ስለሚሆን ህብረተሰቡ የሰላም ጉዳይ የሁላችንም ጉዳይ መሆኑን ተገንዝቦ መሰል ህገ-ወጥ ተግባራትን በማጋለጥ ተባባሪነቱን አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን

@tsegabwolde @tikvahethiopia


Report Page