#ETH

#ETH


ተመርቀው አገልግሎት የማይሰጡ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ለህብረተሰቡ አገልግሎት እንደማይሰጡ ባደረኩት የመስክ ምልከታ አረጋግጫለሁ ሲል የተፈጥሮ ሃብት ፣ መስኖና ኢነርጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገልጿል ፡፡

ለአብነትም የሰቆጣ ፣ ጎንደርና መቀሌ የመጠጥ ዉሃ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ከማይሰጡጥ መካከል ይገኙበታል ብሏል ቋሚ ኮሚቴው፡፡

ከተወካዮች ም/ቤት ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ቋሚ ኮሚቴው ይህን ያለው የውሃ ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴርንና ተጠሪ ተቋማቱን የ2012 በጀት አመት አንደኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸምና የ2012 በጀት አመት እቅድን በገመገመበት ወቅት ነው፡፡

በሰቆጣ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ላይ ያጋጠመው ችግር የጉድጓዱ ውሃ የመስጠት አቅም አነስተኛ መሆኑ ሲሆን ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ወደ ጥናት ተገብቶ የገጸ- ምድር ውሃ ለማምረት እየተሰራ መሆኑን የውሃ ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሽ በቀለ ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይም የጎንደርን የመጠጥ ውሃ ችግር በዘላቂነት የሚፈተው የመገጭ ግድብ ነው ያሉት ሚኒስትሩ ፤ ከአማራ ክልል ውሃ ቢሮ ጋር እየተሰራ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

የመቀሌን የመጠጥ ውሃ ችግር አስመልክተውም ሚኒስትሩ ምላሽ የሰጡ ሲሆን ፣ የፕሮጀክቱ አቅምና ውሃ ፍላጎት አለመጣጣም የፈጠረው ችግር መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ችግሩን ለመፍታትም ከቻይና መንግስት በተገኘ ብድር ጥናት እየተሰራ እንደሚገኝ ዶክተር ኢንጂነር ስለሽ ጠቅሰዋል፡፡

(EPA)

Report Page