#ETH

#ETH


#DIREDAWA

በድሬዳዋ ተከስቶ የነበረውን ሁከትና ብጥብጥ ተከትሎ ለጠፋው የሰው ሕይወትና ንብረት ተጠርጥረው በተያዙ ሰዎች ላይ ክስ ለመመስረት ምርመራ መጀመሩን በኢፌድሪ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታውቋል። የጽህፈት ቤቱ ምክትል ኃላፊ አቶ ረድኤት ግርማ እንደተናገሩት ተከስቶ በነበረው ሁከትና ብጥብጥ እጃቸው አለበት የተባሉ 51 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል የተቀናጀ ምርመራ እየተደረገባቸው ነው።

ተጠርጣሪዎቹ ፍርድ ቤት ቀርበው በጊዜ ቀጠሮ ላይ መሆናቸውንም አመልክተዋል። እንደ ኢዜአ ዘገባ በአቃቤ ህግና በድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን የተቀናጀ ምርመራ የተጀመረባቸው በሰው ሕይወት ማጥፋት፣ በአካል ማጉደል፣ ሃብትና ንብረት በማውደም፣ በግለሰብ ሃብት የእሳት ቃጠሎ በማስነሳትና በሌሎች ክሶች የተጠረጠሩት ሰዎች ላይ ነው፡፡ በሦስት የምርመራ ቡድን የተከፋፈሉ መርማሪዎች ተጨማሪ መረጃና ማስረጃ ከመሰብሰብ ጎን ለጎን በችግሩ ተጠርጥረው ለጊዜው የተሰወሩ ሰዎችን ለመያዝ እየሰሩ መሆናቸውን ነው አቶ ረድኤት የገለፁት፡፡ “እየተካሄደ የሚገኘው ምርመራ እንደተጠናቀቀ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ድሬዳዋ ምድብ ችሎት ክስ ይጀምራል ” ብለዋል፡፡

Via ኢዜአ

@tsegabwolde @tikvahethiopia


Report Page