#ETH

#ETH


አንድ የገቢዎችና ጉሙሩክ ሰራተኛ 3 መቶ ሺ ብር በሙስና ሲቀበል በፖሊስ አባላት እጅ ከፍንጅ ተያዘ። በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው ይርጋ ሃይሌ ገበያ ማዕከል 3ኛ ፎቅ ሉሲ ካፌ ውስጥ ሲሆን ተጠርጣሪው የአ/አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ገቢዎችና ጉሙሩክ ኢንትለጀንስ ሰራተኛ የሆነው የማይገባውን ጥቅም ለራሱ ለማግኘት በማሰብ ግብር ከፋይ ከሆነችው የግል ተበዳይ 3 መቶ ሺ ብር ሲቀበል በፖሊስ አባላት እጅ ከፍንጅ መያዙን የክ/ከተማው ፖሊስ መምሪያ የወንጀልና የትራፊክ አደጋ ምርመራ ዲቪዚዮን ሃላፊ ኮ/ር ጌታነህ በቀለ ተናግረዋል፡፡

የጉዳዩ መርማሪ የሆኑት ኢ/ር ጎይቶም ሃለፎም እንደተናገሩት ተጠርጣሪው ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ሲል የግል ተበዳይን የ2007 እና የ2008 ዓ/ም የግብር ደረሰኝ የከፈለችበት ስህተት ስላለበት ይህ ደግሞ በወንጀል ስለሚያስጠይቅሽ እኔ ላስተካከልልሽ እችላሉ በማለት ከቀጠራት በኋላ ይዛለት የመጣችውን ገንዘብ ተቀብሎ ለመሄድ ሲሞክር በፖሊስ አባላት ከ3 መቶ ሺ ብር ጋር እጅ ከፍንጅ ተይዞ ጉዳዩ በልደታ ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሳኔ እየተጠባበቀ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን

@tsegabwolde @tikvahethiopia


Report Page