#ETH

#ETH


• በኢህአዴግ ውህደት ምክንያት የህዝቡን ሰላም ባያናጉት ጥሩ ነው። ስጋትና አለመረጋጋት መፈጠሩ ለአገሪቱም ጥሩ አይደለም፤ በሚፈጠረው ግጭትም የህዝቡ ደህነት እየከፋ እንዲሄድ ነው የሚያደርገው::

• የኢህአዴግ ውህደት አህዳዊ ስርዓትን ለማምጣት ነው የሚለው ስጋት ከዓለም አቀፍ ተሞክሮ አንጻር አብሮ የሚሄድ አስተሳሰብ አይደለም የሚል እምነት አለኝ።

• ኢህአዴግ አንድ ውህድ ፓርቲ ከሆነ ፌዴራሊዝሙን ያጠፋዋል የሚለው ሀሳብ ቦታ የሌላውና ትርጉም የማይሰጥ ነው።ብዙ የፌዴራል አገሮች አንድ ፓርቲ በምርጫ ተፎካክሮ ካሸነፈ በፌዴራል ስርዓት ስር ያሉ የክልል መንግስታትንም ያስተዳድራል።

• የኢህአዴግ አሰራር አግላይ ነው የነበረው።አራት አህት ድርጅቶች በሚያወጡት ፖሊሲ አባል ያልሆኑት ጭምር ተግባር ላይ እንዲያውሉ ግዴታ ይጥሉባቸው ነበር:: ይህ አካሄድ ኢህአዴግ አሳፋሪ ድርጅት መሆኑን ያሳያል።

• ሁልጊዜ መደራደርና ሰጥቶ መቀበል በፖለቲካው ሂደት ያለ ነገር ነው።አንድ ጊዜ ሲከተሉት የነበረው መስመር ፍጹማዊ አይደለም። ሁሌም የሚሻሻልና የሚቀየር መሆኑን መገንዘብ ያሻል።

• የኢህአዴግ እህት ፓርቲዎች ሁኔታውን ተመልክተው ወደ ስምምነት ቢመጡ ጥሩ ነው የሚል አስተያየት አለኝ። ለአገሪቱ ሰላም መስፈን የጋራ አገራዊ ሀላፊነት አለባቸው።ይህ ሁሉ ታሳቢ ሊያደርጉ ይገባል።

• በዶክተር ዐቢይ የሚመራው ኢህአዴግ እያደረገ ያለው የውህደት እንቅስቃሴ በጣም የዘገየ ነው ባይ ነኝ:: እኛ ቀደም ሲል ኢህአዴጎችን ስንወቅሳቸው ጀምሮ የነበረ ጉዳይ ነው።

• ከ20 ዓመታት በላይ ግንባር እያሉ ሳይዋሀዱ የቆዩት ባይተማመኑ ነው የሚል ሀሳብ ነበረን። በዚህ ሳቢያ ኢህአዴግ ለሌሎች ፓርቲዎች ጥሩ አርአያ አልሆነም።

• ስለዚህ አጋር ፓርቲዎችን በአገሪቱ ጉዳይ ላይ ተሳታፊ ለማድረግ በውህደቱ እንዲካተቱ ማድረግ አስፈላጊና ተገቢም ነው የሚል እምነት አለኝ።

• ኢህአዴግ ውህድ ፓርቲ ሲሆን በየክልል መንግስታት ውስጥ ቅርንጫፎች ይኖሩታል።ለዚህ ጉዳይ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነን የጀርመንና ካናዳ የፌዴራላዊ ስርዓት ነው። የኢህአዴግ ውህደት ዲሞክራሲያዊ ምህዳሩን ያሰፋል እንጂ አህዳዊ ስርዓት የሚያመጣ አይሆንም።

• የኢህአዴግ እህት ድርጅቶች ያላፉት 28 ዓመታት መለስ ብሎ አይተው ቀደም ሲል ሲሰጡ የነበሩትን አመራር አሻሽለው አዲሱን አካሄድ ቢያዳብሩት ነው የሚሻለው። በእልህ አገር አይመራም።እኔ ያልኩት ብቻ ነው እውነት የሚል እሳቤ ከዴሞክራሲያዊ አስተሳሳብ ጋር ግንኙነት የለውም።

• ህገ መንግስት በመጣስ ረገድ ኢህአዴግ ቀዳሚ በመሆኑን እኛ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ስንከሳቸው ኖረናል። ኢህአዴግ ህገ መንግስት አስጠብቃለሁ፤ የአገር መከላከያ ሚኒስቴር ተግባሩ ይህ ነው ይላል::

• ህገ መንግስትን በማክብርና ማስከበር እኛንም ሊያስገድዱን ይፈልጋሉ። ሆኖም አንድ ቁጥር ጣሾቹ እነሱ ነበሩ:: ህገ መንግስቱ የሰጠውን የትም ቦታ ተንቀሳቅሶ የመስራት መብት፣የሰብዓዊ መብት፣የመደራጀት መብትና በነጻነት ሀሳብን መግልፅ መብት ፤ተቃውሞን የማሰማት መብት የሚባሉትን ሁሉ አፎኖ የቆየው በህወሃት የበላይነት ይተዳደር የነበረው ኢህአዴግ ነው።

• በተደጋጋሚ ህገ መንግስት መጣስ የሚባለው ሁሉም እንደሚያመቸው እየተረጎመ ካልሆነ በስተቀር ህወሓትን ጨምሮ ኢህአዴጎች ህገ መንግስቱን በመጣስና ሌላውን በመክሰስ የሞራል የበላይነት የላቸውም።ዕድሜ ልካቸውን ነው ሲጥሱ የቆዩት።ስንት ዓመት ሲያስሩ፣በደል ሲፈጸሙ ነበር።

• እንዲሁም በስብሰናል ማለት የጀመሩት እኮ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ በነበሩ ጊዜ ጀምሮ ነው።አራቱ እህት ፓርቲዎች ሁሉም ነጻ ነኝ የሚል አይኖርም ሁሉም ህገ መንግስቱን ጥሰዋል።

• ስለዚህ በህገ መንግስቱ ውስጥ አንድ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ማህበረሰብ እንፈጥራላን በሚለው ጉዳይም ትኩረት ሰጥተው አልሰሩም።በዚህ ምክንያት ነው በየቦታው ያልጠበቅነው ግጭትና መፈናቀል እየተከሰተ ያለው።

• እንዲሁም በህግ መንግስቱ ተበላሸ የተባለበት ቦታ ለማስተካከል ኃላፊነት ያላቸው ዜጎችና በፖለቲካው አገር እናስተዳድራለን ብለው የተደራጁ ሀይሎች ሀላፊነት አለባቸው::

• ምርጫ በተካሄደ ቁጥር ዘላለም መጨቃጨቅና ውጤቱን አንቀበልም ማለት ከዚያም አልፎ ወደ ግጭት ማምራት የሚያስገባ ነገር ውስጥ እኛ መግባት አንፈልግም።

• ምርጫ ማለት ሰላማዊ ተግባር ነው እንጂ ህዝባችን ምርጫ በመጣ ቁጥር ጦርነት እንደታወጀበት ነው እስካ ዛሬ እየቆጠረ ያለው:: እኛ ይህ ስርዓት ይይዛል ወይ የሚለው ጉዳይን ለማየት እየናፈቅን ነው ያለነው።

• የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስተካከል ተግተን መንቀሳቀስ አለብን። የፖለቲካ ምህዳሩ መስፋት አገራዊና ህዝባዊ ፋይዳ ያለው ጉዳይ ነው።ከምርጫ በስተቀር ሌላ የሚያስተማምነን የለም::

• ህዝቡ ይሁንታ የሰጠው አገሪቱን እንዲመራ፤የተሸነፈው ደግሞ ለሚቀጥለው የምርጫ ጊዜ ተሽሎ ለመገኘት መስራት አለበት:: ይህ ሲሆን ነው የዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ መሰረት ተጣለ የሚባለው ።

• ለዚህ ደግሞ ሁላችንም ተግተን መስራት አለብን። ግማሹ ተቀምጦ የት ደረሳችሁ የሚልበት ሳይሆን ከዚህ ጉዳይ የሚበልጥብኝ የለም፤ በአገር ሰላም እንዲሰፍን፤መረጋጋት እንዲፈጠር፣ልማትና ዕድገት እንዲመጣ ሁሉም ይፈልጋል።ይህ ተቀምጦ አይገኝም።

• ስለዚህ ህዝቡ ድምጹን ማሰማት መጀመር አለበት። ተገቢው እርምጃ የማይወስደውን፣ ያለመጠውን፣ አልባሌ ነገር ውስጥ መግባት የሚያምረውን ሁሉ መገሰፅ አለበት።በዚህ መልኩ ከተሰራ ብርሃን ይፈነጥቃል።

ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስን

Report Page