#ETH

#ETH


የኦሮሚያ ክልል መንግስት...

ባለፈው ሳምንት ከተደረጉ ሰልፎች ጋር በተያያዘ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ተፈጥሮ የነበረው ግጭት መረጋጋቱ እና ሕዝቡም ወደ የዕለት ተዕለት ሕይወቱ መመለሱን የኦሮሚያ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ገልጿል። ግጭት ተፈጠሮባቸው በነበሩ አካባቢዎች በደህንነት ስጋት አካባቢዎቹን ለቀው የሸሹ ሰዎች ወደየመኖሪያ አካባቢያቸው መመለሳቸውም ተገልጿል።

በእነዚህ አካባቢዎች ችግሩ እንዲቀጥል የሚፈልጉ አካላት ቢኖሩም በህዝቡና በጸጥታ አካላት ትብብር ሃሳባቸው ሊሳካ እንዳልቻለም ነው ቢሮው የገለጸው። ዘር እና ሃይማኖትን ከለላ በማድረግ በሕዝቦች መካከል ግጭት በመፍጠር የተጠረጠሩ አካላት በሕዝቡና በፀጥታ ኃይሎች ትብብር እና ድጋፍ ለሕግ እየቀረቡ መሆኑም ተጠቁሟል። መንግሥት የእርስ በርስ ግጭቱን በመፍጠር ሚና የነበራቸው አካላት ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ እና በክልሉ የሕግ የበላይነትን ለማስከበር የጀመረውን ሥራ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል።

ሕዝቡ እያደረገ ያለውን ትብብር አጠናክሮ መቀጠሉ መንግሥት ሰላምን እና የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በሚያደርገው ጥረት ውስጥ ወሳኝ መሆኑን የኦሮሚያ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮን ጠቅሶ የዘገበው ኦቢኤን ነው።

Via OBN

@tsegabwolde @tikvahethiopia


Report Page