#ETH

#ETH


የደቡብ ክልል ፣ የጋሞ ዞንና የኦሮምያ ክልል ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የሀገር ሽማግሌዎች ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል በተፈጠረው ሁከት በሰበታ ከተማ የደረሰውን ጉዳት አስመልክቶ በቦታው በመገኘት በደቡብ ክልል ተወላጆች ላይ ስለደረሰው ጉዳት ከሰበታ ከተማ አስተዳደር አመራሮች ጋር ውይይት አካሂደዋል፡፡ በደረሰው ጉዳት የተሳተፉ 48 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ተጠቁሟል

*****************//****************

ሰሞኑን በኦሮምያ ክልል አንዳንድ አከባቢዎች በተፈጠረው ረብሻ በሰዎች ህይወት እና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ይታወቃል ፡፡

በዚህ ከተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች በሰበታ ከተማ ቀበሌ 03 የሚገኙ የደቡብ ክልል ተወላጆች ሲሆኑ በደረሰው ጉዳትና ቀጣይ መሰራት ባለበት ተግባር ዙርያ ለመወያየት በደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር በአቶ እርስቱ ይርዳ የተላከው ቡድን ከኦሮምያ ክልል በአቶ ካሳሁን ጎፌ የኦዴፖ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት የከተማ ፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ ከተመራ ቡድን ጋር በደረሰው ጉዳት እና ቀጣይ መከወን በሚገባቸው ተግባራት ዙሪያ በዝርዝር ተወያይተዋል፡፡

በተፈጠረው ችግር ከተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በመወያየት ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ የተደረገ ሲሆን ቤት ለተቃጠለባቸው 15 አባወራዋች መልሶ ለመገንባት አስፈላጋውን ዠግጅት ከተማ አስተዳደሩ ያጠናቀቀ ሲሆን ቤቱ ተገንብቶ እስከሚጠናቀቅ ለተፈናቃዮች ከተማ አስተዳደሩ የኪራይ ቤት ለማመቻቸት እየሰራ መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል።

በቀጣይ ተመሳሳይ ችግር እንዳይደርስ የከተማ አስተዳደሩ ሀላፊነት በመውሰድ ከህብረተሰቡ ጋር በቅርበት እንደሚሰራ ቃል የገባ ሲሆን በዚህ እኩይ ተግባር የተሰማሩ 48 ተጠርጣሪዎች እስካሁን በቁጥጥር ሰር የዋሉ ሲሆን በቀጣይም ህግ የማስከበሩ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ከተማ አስተዳደሩ አረጋግጧል፡፡

ከተማ አስተዳደሩ ህብረተሰቡ ካነሳቸው ስጋቶች አንዱ በአቅራብያቸው የፖሊስ ተቋም አለመኖሩ መሆኑን በመገንዘብ 7አባላት ያሉት የፖሊስ ቡድን በትላንትናው እለት በአቅራብያቸው እንዲመደብ ተደርጓል።

የሰብአዊ እርዳታንም በተመለከተ በቀበሌያቸው እንደሚቀርብ አረጋግጧል።

በመድረኩም ሰላም ለሁሉም ህብረተሰብ ቅድሚያ አጀንዳ ሊሆን የሚገባው በመሆኑ ሰላምን ለማረጋገጥ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ አጽዕኖት ተሰጥቶታል።


Report Page