#ETH

#ETH


#HAWASSA

የሀዋሳ ከተማ ም/ቤት በ2ኛ ዙር፣ 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 12ኛ መደበኛ ጉባኤው የካቢኔ አባላትን ሹመት አፅድቋል።

በም/ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ አማካይነት የቀረቡት የአስተዳደሩ የካቢኔ አባላት የትምህርት ዝግጅታቸው እና የስራ ልምዳቸውን ታሳቢ ያደረገ እንደሆነም ተገልጿል።

በዚህም፦

1. አቶ መልካሙ ወርቁ የሀዋሳ ከተማ ም/ከንቲባ እና የትምህርት መምሪያ ኃላፊ፣

2. አቶ ሽታዬ ጫቡላ የሀዋሳ ከተማ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ

3. ወ/ሮ ዘውዲቱ ገ/መስቀል የሀዋሳ ከተማ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ፣

4. አቶ ታምሩ ተፈሪ የሀዋሳ ከተማ ገቢዎች ባለስልጣን ቅርንጫፍ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣

5. አቶ ብርሃኑ ሌታሞ የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት መምሪያ ኃላፊ፣

6. ኮ/ል ሮዳሞ ኪአ በአስተዳደሩ የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ፣

7. አቶ ኃይሉ የተራ በአስተዳደሩ የኢንተርፕራይዝና የኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ ኃላፊ፣

8. አቶ አፈወርቅ አለማየሁ በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ኃላፊ፣

9. አቶ ፍቅረየሱስ አሸናፊ የግብርና መምሪያ ኃላፊ እና

10. አቶ ጎሳዬ ጎዳና የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ኃላፊ ሆነው እንዲሰሩ ለተከበረው ም/ቤት የቀረቡ ሲሆን የም/ቤቱ አባላትም በመሉ ድምጽ ተቀብሎ አፅድቋል።

በተመሳሳይም የተከበረው የከተማዋ ም/ቤት የመጨረሻ በሆነው አጀንዳው የቋሚ ኮሚቴ ሹመትንም ተቀብሎ በማፅደቅ ተጠናቋል።

Hawassa City Administration Public Relation Office

Report Page