ETH

ETH

ቲክቫህ ኢትዮጵያ

በቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ እያከናወናቸው ካሉ ዝግጅቶች መካከል አንዱ የምርጫ ቁሳቁሶችን ማሟላትና ደኅነቱን የጠበቀ እንዲሆን ማስቻል ነው፡፡ ለመሆኑ በቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ በዚህ ዙሪያ ምን ልዩ የሆነ ነገር ልንመለከት እንችላለን?



በመራጮች ምዝገባ ወቅት



የመራጮች መዝገብ ከዚህ ቀደም ካለው በተሻለ የደኅንነት መጠበቂያዎች እንዲኖሩት ተደርጓል፡፡ በዚህም እያንዳንዱ መራጭ የራሱ መለያ ቁጥር ይኖረዋል፣ መራጮች ከሚወስዱት ካርድ በተጨማሪ በመዝገቡ ቀሪ ይኖራል፣ በቀላሉ ተመሳስሎ እንዳይሰራ ተደርጎ የተዘጋጀ ነው፡፡

ምዝገባው ከተጠናቀቀ በኀላ መከፈቱ በሚያሳውቅ ቦርሳ ወኪሎችና ታዞቢዎች በተገኙበት ታሽጎ ዝውውር ይደረጋል፡፡ ይህ ሲካሄድ ልዩ መለያ ቁጥር ባላቸው ሶጥኖች ተደርጎ በመሆኑ በሚያጠራጥሩ ሳጥኖች ላይ ምርመራ ይደረጋል፡፡



በድምጽ መስጫ ወቅት



እያንዳንዱ የድምጽ መስጫ ወረቀት ለጊዜው ያልተገለጹ የደኅንነት መጠበቂያ የተደረገባቸው ናቸው፡፡ ልዩና ሚስጢራዊ ማህተም ይደረግባቸዋል፣ ቆጠራ የሚደረግባቸውም እነዚሁ የድምጽ መስጫ ወረቀቶች ብቻ ናቸው፡፡ 



በግልጽ የሚያሳይ የድምጽ መስጫ ሳጥን ሌላው ከዚህ ቀደም የነበረውን ኮሮጆ የተካ ነው፡፡ ሳጥኑ ድምጽ መስጠት ከመጀመሩ በፊት ቦዶ መሆኑን በቀላሉ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ እያንዳንዱ ሳጥን ልዩ መለያ ቁጥር ያለው ሲሆን ሲዘጉና ሲከፈቱ የማሸጊያ ቁጥራቸው ይመዘገባል፡፡ 800 -1500 ድምጾችን መያዝ አቅም አለው፡፡ 



ከዚህ ቀደም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ለክልል ምክር ቤት የሚሰጡ ድምጾች በአንድ ኮሮጆ ተሰብስበው በቆጠራ ወቅት የሚለዩ ሲሆን አሁን ግን በተለያዩ ሳጥኖች ድምጹ የሚሰጥ ሲሆን ሳጥኖቹም በቀለም ይለያያሉ፡፡

የሚስጥር ድምጽ መስጫ መከለያዎች ከዚህ ቀደም በመጋረጃ እንዲሁም በተለያዩ ነገሮች በመከለል የሚደረግ የነበረውን በመተካት በቀላሉ የሚገጣጠሙ በሚስጥር ድምጽ መስጠት በሚያስችል መልኩ የተዘጋጁ ናቸው፡፡ 

በምርጫ ጣቢያዎች የሚሰቀሉ ማሳወቂያዎች፣ ጠቋሚዎች፣ ልዩ ልዩ ምልክቶች ከዚህ ቀደም ወረቀት በመሆናቸው በቀላሉ ጉዳት ሲደርስባቸው ቆይቷል ይህንን ለመቅረፍም ስቲከሮችንና የጨርቅ ህትመቶች ተዘጋጅተዋል፡፡

ከዚህ ባለፈ በመራጮች ምዝገባ ወቅት እንዲሁም በድምጽ መስጫ ወቅት የሚያገለግሉ የተለያዩ የጽሕፈት መሳሪያዎች፣ ባትሪዎች፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች መለያ ልብሶችና መታወቂያዎች ምርጫ ቦርድ ግዢ ፈጽሞባቸው ባሉት የተለያዩ ማዕከላት በልዩ ጥበቃ ስር ያሉ ናቸው፡፡

Report Page