#ETH

#ETH


ትናንት በአምቦ ከተማ ከተገደሉት ሶስት ሰዎች በተጨማሪ ዛሬ ሁለት ሰዎች ተገድለዋል። ዛሬ የጥይት ሰለባ ከሆኑት መካከል የ80 ዓመቱ አዛውንት አቶ ሞሮዳ የሚባሉ ይገኙበታል። አቶ ሞረዳ ልጃቸውን ፍለጋ በወጡበት ከጸጥታ አስከባሪ ኃይል በተተኮሰባቸው ጥይት መገደላቸውን የከተማው ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል።በአምቦ ዛሬ ከተገደሉት ሁለት ሰዎች በተጨማሪ ሌሎች በርካታ ሰዎቸ በጥይት ተመትተዋል። የአምቦ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር አቶ ደበበ ፈጠነ፤ "ዛሬ 14 ሰዎች በጥይት ተመተው እኛ ጋር መጥተዋል። ሁለቱ ህይታቸው አልፏል። 9 ሰዎች ደግሞ ተኝተው እየታከሙ ሲሆን የተቀሩት ቀላል ህክምና ተደርጎላቸው ወደየቤታቸው ተመልሰዋል" በማለት ያስረዳሉ።አቶ ደበበ ወደ ሆስፒታላቸው የመጡት ሰዎች በሙሉ ወንዶች መሆናቸውን እና ዕድሜያቸውም ከ17-80 እንደሚገመት ተናግረዋል። በዚህም በአምቦ ትናንት 3፤ ዛሬ 2 በድምሩ የሟቾች ቁጥር 5 ደርሷል።ምስራቅ ሃረርጌ በሁለቱ ቀናት በምስራቅ ሃረርጌ በተካሄዱት ሰልፎች የሟቾች ቁጥር 6 መድረሱን ሰምተናል።

በዞኑ የኮሚኒኬሽን ባለሙያ የሆኑት አቶ አየለ ዴሬሳ በምስራቅ ሃረርጌ በሚገኙ ከተሞች ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደው እንደነበረ ተናግረው፤ በሁለት ከተሞች በተፈጠረው ግጭት የ6 ሰዎች ህይወት ማለፉን እና በተቀሩት ከተሞች ግን የተካሄዱት የተቃውሞ ሰልፎች በሰላም መጠናቀቃቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ አየለ፤ ትናንት 5ቱ ሰዎች የተገደሉት ጉሮ ጉቱ በምትባል ከተማ ወደ ብሄር በተቀየር ግጭት ስለመሆኑ ይናገራሉ። "አንድ ባለሃብት የደህንነት ስጋት ተሰምቶት ሁለት ሰዎችን በጥይት መትቶ ገደለ። ከዚያም በቂም በቀል ግለሰቡ እና ሁለት የቤተሰብ አባላቱ ተገደሉ" ሲሉ ሁኔታውን ያስረዳሉ። የአወዳይ ከተማ ነዋሪ የሆነ ወጣት ከመከላከያ ሠራዊት በተተኮሰ ጥይወት ስለመገደሉ የአወዳይ ከተማ ክንቲባ ጃፋር ሙሐመድ ለቢቢሲ ተናግረው ነበር።

Via BBC

Report Page