#ETH

#ETH


​​#ADAMA

የኢትዮጵያ መንግሥት የጸጥታ ኃይሎች የኦሮሞ አክቲቪስት እና የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ቴሌቬዥን (OMN) ጣቢያ ዋና ዳይሬክተር ጀዋር መሐመድን መኖሪያ ቤት አቅራቢያ ተሰማርተዋል መባሉን ተከትሎ በአብዛኞቹ የኦሮሚያ ከተሞች ውጥረት ነግሷል። ድርጊቱን በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ እየተደረገባቸው ካሉ የኦሮሚያ ከተሞች መካከል አንዱ በሆነችው አዳማ አንድ ሰው መሞቱን እና ንብረት መውደሙን የዓይን እማኞች ተናግረዋል። በአዳማው ተቃውሞ ከየት እንደተተኮሰ ባልታወቀ ጥይት የአንድ ግለሰብ ህይወት ማለፉን በአካባቢው የነበሩ የዓይን እማኞች ገልጸዋል።

የአዳማ ከተማ ከንቲባ አቶ አሰግድ ጌታቸው የችግሩን መፈጠር አምነው የተጣራ መረጃ በእጃቸው እንደሌለ ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ተናግረዋል። ከአዳማ ሌላ በበርካታ የኦሮሚያ ከተሞች መንገድ ተዘግቷል። በአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ ያሉ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከተሞችም ተቃውሞውን ተቀላቅለዋል።

በአራቱም አቅጣጫ ወደ አዲስ አበባ የሚያስገቡ መንገዶችም መዘጋታቸውን በየአካባቢዎቹ ያሉ ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬለ አረጋግጠዋል። በአዳማ፣ ጅማ እና ሀረር ከተሞች ለተቃውሞ የወጡ ሰልፈኞች «ጃዋርን የሚነካ ማን ነው?» የሚሉ መፈክሮችን ሲያስተጋቡ መደመጣቸውን የአይን እማኞች ጠቁመዋል።

Via የጀርመን ድምፅ ሬድዮ/DW/

PHOTO: Tikvah Family

@tsegabwolde @tikvahethiopia


Report Page