#ETH

#ETH


•ሁለት ሰው ሞቷል

•ከ50 በላይ ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል

በአዳማ ከተማ ዛሬ በተከሰተው የፀጥታ ችግር የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉንና በ50 ሰዎች ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አስታውቋል። የአዳማ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ደረጀ ሙለታ ለኢዜአ እንዳሉት በከተማዋ ዛሬ ጠዋት ላይ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ከተለያዩ አቅጣጫዎች የተሽከርካሪ መተላለፊያ መንገድ ሲዘጋ ነበር።

በዚህም ተሳትፎ የነበራቸው ግለሰቦች ድንጋይ መወርወር ፣ንብረት ላይ ጉዳት ማድረስና የተለያዩ የንግድ ተቋማትን የመዝጋት ችግር እንደፈጠሩ ተናግረዋል። የከተማው ፖሊስ አባላት የሰው ህይወት እንዳይጠፋና ንብረት እንዳይወድም ለመከላከል ጥረት ማድረጋቸውን አስረድተዋል። ሆኖም ከተከሰተው የጸጥታ ችግር ተያይዞ በተፈጠረው ግርግር የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን ኮማንደሩ አስታውቀዋል። 50 ሰዎች ደግሞ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በአዳማ ሪፈራል ሆስፒታልና ሜዲካል ኮሌጅ የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን አመልከተዋል።

“በአሁኑ ወቅት ከተማዋን የፀጥታው ሁኔታ ወደ ነበረበት ለመመለስ የተለያዩ የፀጥታ አካላት ገብተው በጋራ እየሰሩ ነው “ብለዋል። “ሁሉም ዜጋ ለሰላም፣ ዘብ መቆም አለበት ያሉት ኮማንደሩ ማንኛውም ጥያቄ ቢኖር በሰላማዊ መንገድ ብቻ በመጠየቅ የከተማዋን መልካም ስም ለማስጠበቅ ነዋሪው የድርሻውን እንዲወጣም ጠይቀዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ

@tsegabwolde @tikvahethiopia


Report Page