#ETH

#ETH


ለጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ እና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ በቀረቡላቸው ጥያቄዎች ላይ የሰጧቸው መልሶች

- በክልሎች መካከል ያለው የትጥቅ እና የቃላት ፉክክር የመጣው ከባለፈው ችግር ካለመማር እና ከባለፈው ወረት ካለመጠቀም ነው፡፡

- ዓለም ከአንደኛው የዓለም ጦርነት ባለመማሯ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት መከሰቱንም በምሳሌነት አንስተዋል።

- አሁን ያለው ችግር ምን ዓይነት ውጊያ ይገጥመናል የሚለውን ካለመገንዘብ ነው ካሉ በኋላ ለዚህ ችግር ዋነኛ ምክንያት የሆኑት “ዕድሜ ጠገብ ፓርቲዎች እና ሰዎች” እንደሆኑ ተናግረዋል።

- “እነዚህ ወገኖች ወጣቶችን ያስገድላሉ እንጂ መሞት አያውቁበትም” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ መፍትሔ የሚገኘው በክላሽ ነው የሚሉትን ሰዎች ወጣቱ "በቃችሁ፣ ጡረታ ውጡ" ሊላቸው ይገባል በማለት አሳስበዋል።

- ከትላንት መቆሳሰል፣ ከትላንት መገዳደል፣ ከትላንት ኪሳራ መማር የቻለ ሰው መልሶ ወደዚያ አይመለስም ሲሉም አክለዋል።

- አሁን በአማራ እና በትግራይ ክልል መካከል እየታየ ያለው ሁኔታ ልክ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ተገዳድለው በኋላ ላይ እንዳፈሩበት አይነት ነው፤ ሌላ ምንም አይጠቅምም።

- በአማራ እና በትግራይ ሕዝብ መካከል ግን መቼም መለያየት አይኖርም ብለዋል።

- በአማራ እና በቅማንት መካከል በድንበር መለየት የማይቻል፣ አንዳንድ ቦታ ደግሞ በቤተሰብ እንኳን መለየት የማይቻል እንደሆነ ተናግረዋል።

- ነገር ግን አሁን ላይ እየታዩ ባሉ ግጭት ውስጥ እሳት ለኩሰው እየሞቁ መኖር የሚቻል የሚመስላቸው ሊኖሩ እንደሚችሉ ገልጸዋል።

- ኃላፊነት ላለመውሰድ ሲባል እኛ አይደለንም ሌላ ነው የሚያጋጨን የሚባል ከሆነ ግን ይህን መንግሥት ሊፈታ አይችልም ብለዋል።

- ለቅማንት ሕዝብ ከአማራ ሕዝብ በበለጠ ማንም የሚቀርበው ሕዝብ አለመኖሩን እና በሁለቱ ሕዝቦች መካከል በሚፈጠረው ግጭት ሰዎች ይሞታሉ እንጂ የአማራ እና የቅማንትን ሕዝብ መቼም የሚለያይ ሕዝብ አለመሆኑንም አክለዋል።

- መንገድ መዝጋት የኋላ ቀር ፖለቲካ እና ጥሩ ባህል አለመሆኑን ገልጸዋል።

- እኛ ሀገር መንገድ መዝጋት ብቻ ሳይሆን ሰዎች አዳራሽ ውስጥ በሚሰበሰቡበት ወቅት ገብቶ የመረበሽ ሁኔታ እንዳለ እና ያ ግን አግባብ እንዳልሆነ ተናግረዋል።

- “መንገድ ዘግተን አንድ ሺህ ሰው በማንገላታት አንድ ሚሊዮን ሰው ማስቆጣት የለብንም።” ሲሉም አሳስበዋል።

- በዘንድሮ የዝናብ አቅርቦቱ የተሻለ በመሆኑ በአገሪቱ ከፍተኛ የግብርና ምርት ይጠበቃል፡፡

- በዚህ ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የግብርና የውጭ ንግድ እቅድ 101 በመቶ ተሳክቷል፡፡

- በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ኢትዮጵያ በአፍሪካ ትልቅ ኢኮኖሚ ትገነባለች፡፡

- ኢትዮጵያ በቱሪዝም ሰፊ አቅም ያላት በመሆኑ በዘርፉ አገሪቱና ህዝብ ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው፡፡

- ለአብነትም በስድስት ወር በተጠናቀቀው የአንድነት ፓርክ ለበርካታ ሰዎች የስራ እድል ከመፍጠር ባለፈ ስፍራውን በቀን ብዙ ሺህ ሰዎች እየጎበኙት ነው፡፡

- ከውጭ የሚመጡ ቱሪስቶች በአገሪቱ እንዲቆይና ደግመው እንዲመጡ በቱሪዝም መዳረሻዎች ላይ የተለያዩ መሰረተ ልማት ለማሟላት ጥረት እየተደረገ ነው፡፡

- በዘንድሮ ዓመት ብቻ 4 ትላልቅ ኮንፈረንሶች በኢትዮጵያ የሚካሄዱ ሲሆን ፓርላማው የዘርፉን ስራ በመቆጣጠር ድጋፍ ሊያደርግ ይገባል፤ በተለይ የሆቴል ባለሀብቶች ደግሞ ስራቸውን በቅርበት መስራት ይገባቸዋል፡፡

- በአዲስ አበባ የተለያዩ ፓርኮችን ማስፋት ሲቻል የተለያዩ መዝናኛ ስፍራ ከመፍጠር ባለፈ በስፋት የቱሪዝም መዳረሻዎች እንዲኖሩ ማድረግ ይቻላል፡፡

- የአገሪቱን በጀት የሚያባክኑና የሚሰርቁ የመንግስት አመራሮች በህግ ይጠየቃሉ፡፡

- የእንስሳት የመኖ እጥረትን ለመፍታት በዝቅተኛ ስፍራ በመስኖ ልማት የመኖ ልማት በማከናወን የአቅርቦት ችግሩን ለመፍታት እየተሰራ ነው፡፡

- የቁም እንስሳት የውጭ ንግድ በመቀነስ በአገር ውስጥ ምርቱን በማቀነባበር ወደ ውጪ ለመላክ እየተሰራ ነው፡፡

- በአገሪቱ የኑሮ ውድነት የሚያመጡ የቤት ኪራይ፣ የፍጆታ ምግብ፣ ስራ አጥነት፣ የምርት አቅርቦት እጥረት በመሆናቸው እነዚህን ችግሮች ለማቃለል የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ነው፡፡

- ለጎዳና ተዳዳሪዎች ከ4 ሺህ እስከ 5 ሺህ ቤቶች ይገነባሉ፡፡

ETV

Report Page