#ETH

#ETH


ከ687 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዙን የጉምሩክ ኮሚሽን ገለፀ!

ባለፈው ሩብ ዓመት ግምታዊ ዋጋቸው 687ሚሊየን ብር በላይ የሆኑ ገቢና ወጭ ኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዙን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ ኮሚሽኑ በቁጥጥር ስር ካዋላቸው መካከል የጦር መሳሪያዎች ፣የተለያዩ አገራት ገንዘቦች፣ መድሃኒቶች ፣አደንዛዥ እፆች ፣ምግብ ነክ ሸቀጣ ሸቀጦች ፣ኤሌክትሮኒክስና ልዩ ልዩ መለዋዎጫ እቃዎች እንዲሁም ልባሽና አዳዲስ ጨርቆች ፣ወደ አገር እንዳይገቡ ክልከላና ገደብ የተደረገባቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ይገኙበታል፡፡

ኮሚሽኑ እንዳስታወቀው የኮንትሮባንድ እቃዎች ከዓምናው ተመሳሳይ ወቅት ከተያዙት እቃዎች ጋር ሲነፃፀር የ489 ሚሊየን ብር ግምታዊ ዋጋ ብልጫ አላቸው፡፡

በቀጣይም ኮንትሮባንድ እና ህገ ወጥ ንግድ ላይ የተጠናቀረ የህግ ማስከበር ስራ እንደሚሰራና ወጭ እና ገቢ ንግዱም የተቀላጠፈ እንዲሆን የአሰራር ስርዓቶችን ዘርግቶ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነሩ አቶ ደበሌ ቃበታ ዋቢ በማድረግ የገቢዎች ሚኒስቴር ያወጣው መረጃ ያመለክታል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia


Report Page