#ETH

#ETH


በሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን ስም የተቋቋመው የባህል ማዕከል ተከፈተ!

-የሎሬቱ ሀውልት በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሊቆምላቸው ነው

በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ በሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን ስም የተቋቋመው የባህል ማዕከል ተከፈተ። የሎሬቱ ሀውልት በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሊቆምላቸው ነው።

ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን አምቦ ካበቀለቻቸው ባለ ምጡቅ አዕምሮ መካከል በስነፅሁፍና በትያትር ዘርፍ በፈርጥነት የሚጠቀሱ ምሁር ቢሆኑም፤ በሚገባቸው ልክ ክብር እንዳለተሰጣቸው በሎሬቱ ስም ዛሬ በአምቦዩኒቨርሲቲ የመታሰቢያ የባህል ማዕከል በተከፈተበት ወቅት ተገልጿል።

የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ታደሰ ቀና እንዳሉት፤ ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን የጥበብ ሰው ብቻ ሳይሆኑ የሰብአዊ መብትሟጋች ነበሩ። በስራዎቻቸው በሀገራቸው የተዘጉትን ታሪካዊና ማህበራዊ መስተጋብሮች ሲተቹና እንዲስተካከሉ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ሲያደርጉ ነበር፡፡

በዩኒቨርሲቲው የተቋቋመው የባህል ማዕከል ሁለት አላማ ያለው ሲሆን፤ አንዱ አዲሱ ትውልድ ታላላቆቹን እንዲያውቅ፣ የሰሩትን ስራ እንዲረዳና አዳዲስ ሀሳቦችን ማፍራት እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ በበኩላቸው፤ ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን በወቅቱ ክብር ይናፍቀኛል ተቻችሎ የሚኖር ህዝብ ያስቀናኛል ድንቁርና ያስፈራኛል ጦርነት ያስጠላኛል ሲል ህብረብሄራዊ አንድነትን ፣ብልፅግናና ሰላምን የሰበኩ የጥበብ ሰው ናቸው፡፡ዛሬ ለሀገራችን የሚያስፈልጋትም ይህ ነው ብለዋል፡፡

በዕለቱም አንጋፋ አርቲስቶች ፣ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲ መምህራን፣ የሎሬቱ ቤተሰቦች፣ የሀይማኖት አባቶች፣የሀገር ሽማግሌዎችና አባ ገዳዎች የተገኙ ሲሆን ለማዕከሉ ማደራጃና ለሚቆመው ሀውልት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል፡፡

Via EPA

Report Page