#ETH

#ETH


የቡኖ በደሌ ዞን ነዋሪዎች የመሰረተ ልማት ችግር እንዲፈታላቸው ጠየቁ!

በኦሮሚያ ክልል የቡኖ በደሌ ዞን ነዋሪዎች በአካባቢያቸውን የሚታየውን የመሰረተ ልማት ችግር እንዲፈታላቸው ጠየቁ።

የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ መንግስት የምዕራብ ኦሮሚያ አካባቢዎች በልማት በኩል ያሉባቸውን ችግሮች በመገንዘብ ደረጃ በደረጃ ለመፍታት ጥረት እያደረገ መሆኑን አስረድተዋል።

የቡኖ በደሌ ወረዳ ነዋሪዎች የልማት ጥያቄአቸውን ያቀረቡት ትናንት ከክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው።

ከዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች የተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች የክልሉ መንግስት ያሉባቸውን የልማት ችግሮች   እንዲፈታላቸው ጠይቀዋል።

በውይይቱ ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል መንግስት በየጊዜው የሚቆራረጠው የመብራት አገልግሎት በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ተፅዕኖ እያሳደረ በመሆኑ በአፋጣኝ ሊፈታልን ይገባል ብለዋል።

የበደሌ ሆስፒታል ለአካባቢው ማህበረሰብ የተሟላ የህክምና አገልግሎት እንዲሰጥ ወደ ሪፈራል ሆስፒታል እንዲያድግላቸውም ነዋሪዎቹ ጠይቀዋል።

የመቱ ዩኒቨርስቲ የበደሌ ግብርናና ደን ሳይንስ ኮሌጅ ወደ ሙሉ ዩኒቨርስቲነት እንዲያድግላቸውም ነዋሪዎቹ ለምክትል ፕሬዚዳንቱ አንስተውላቸዋል።

በአካባቢው ለቡና ፣ አትክልትና ፍራፍሬና ለማር ምርት ያለውን አመቺነት በመጠቀም አርሶአደሩ ምርቱን ለውጭ ገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ እንዲሆን መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍና እገዛ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

ወደ ዴዴሳ ወረዳ በሰፈራ መልክ የመጡና በቂ መሬት ያላገኙትን አባወሯዎች ችግር ለመፍታትም የክልሉ መንግስት እየሰራ በመሆኑ በአጭር ጊዜ ውስጥ ችግሩ እንደሚቀረፍ አስረድተዋል።

Via ENA

@tsegabwolde @tikvahethiopia


Report Page