#ETH

#ETH


የስራ ማስታወቂያ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቅርቡ ለሚያካሂደው የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ የተለያዩ ዝግጅቶችን እያደረገ ሲሆን በዚሁ ስራ ይረዳ ዘንድ ለአጭር ጊዜ የፕሮጄክት አስተባባሪ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

የስራ መደቡ መጠሪያ - የፕሮጄክት አስተባባሪ

የስራ ጊዜው - የአጭር ጊዜ ማስተባበር (21 ቀናት)

የስራ መደቡ ዋና ዋና ሃላፊነቶች

-ለሲዳማ ሪፈረንደም አፈጻጸም ፕሮጄክት ስራ የማስተባበር ድጋፍ መስጠት

-ከቦርዱ የምርጫና ሎጀስቲክስ ክፍል ጋር በመተባበር የምርጫ ዝግጅቱን እና ሂደቱን ማገዝ

-አስፈላጊ ከሆኑ የተለያዩ አካላት ጋር ግንኙነቶችን ማድረግና ስራዎች በእቅድ መሰረት መፈጸማቸውን ማረጋገጥ

-የሲዳማ ህዝበ ውሳኔን የሚመለከቱ ውይይቶችን እና ሁነቶችን ማዘጋጀት፣ማስተባበር

-አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከቦርዱ የሚፈለጉ መረጃዎችን ለሚመለከታቸው አካላት መስጠትና በተመሳሳይም ለቦርዱ የሚያስፈልጉ መረጃዎችን ማጠናከር

-የስራውን ሂደት እና ውጤት አስመልክቶ ከቦርዱ የምርጫና ሎጀስቲክስ ክፍል ጋር በመተባበር ሪፓርት ማጠናከር

ተፈላጊ ችሎታ

-የመጀመሪያ ደረጃ ዲግሪ

-ቢያንስ ለ5 አመት ያህል የማስተባበር ስራ ልምድ

-የምርጫ እና ተያያዥ ሂደቶችን በሚገባ የሚረዳ/የምትረዳ

-በፍጥነት ችግሮችን የመፍታት ክህሎት ያለው/ያላት

-በአጭር ጊዜ የማስተባበር ስራዎችን የመስራት ልምድ ያለው/ያላት

-መረጃዎችን መሰብሰብና ሪፓርት ማጠናቀር ልምድና ችሎታ ያለው/ያላት

-የፌደራሉን የስራ ቋንቋ በሚገባ መጻፍና መናገር የሚችል/የምትችል፣ (ተጨማሪ ቋንቋ ማወቅ ይበረታታል)

ክፍያ - በስምምነት

ለማመልከት - ለስራው ማመልከት የሚፈልጉ አመልካቾች ሲቪ እና የተጠቀሱትን ችሎታቸውን የሚገልጽ ሸኚ ደብዳቤ በማዘጋጀት የሚልኩት ኢሜል ርእስ ላይ ፕሮጄክት አስተባባሪ የሚል በመጻፍ electionsethiopia@gmail.com መላክ ይችላሉ፡፡

የማመልከቻ ጊዜ - ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ3 የስራ ቀናት ብቻ

Report Page