#ETH

#ETH


‹‹ትብብርና ፉክክር ሚዛናዊ መሆን አለባቸው!›› አቶ ዮናስ ዘውዴ

ሀገራችን በብዙ ርዕዮተ ዓለም ሙከራ ውስጥ ብትቆይም እስካሁን ድረስ የምዕራቡን አስተሳሰብ ስንቃርም ቆይተናል፡፡ አሁን ላይ መደመር ሀገራዊ መፍትሔን ይዞ መጥቷል፡፡ መደመር የሰው ልጅ ምንድን ነው ብሎ ይጠይቃል እንዲሁም የሰውን ልጅ ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆኑ የህልውና ፍላጎቶችን በመመለስ ያምናል፡፡

መደመር መጨፍለቅ ማለት አይደለም መደመር አሀዳዊነትም ማለት አይደለም መደመር የተበታተነ አቅምን ወደ አንድ ማምጣት ማለት ነው፡፡ የመደመር መነሻ ከነበረው ነገር ላይ ነው፡፡ የተሰሩ ሥራዎችን ንዶ እንደ አዲስ አይገነባም ነገር ግን ያሉትን ይዞ ክፍተታቸውን ይሞላል እንጂ፡፡

ትላንትናዎቻችን ክፉ ብቻ አይደሉም በጎ ነገሮችም አሉት ደግሞም በጎ ብቻ አይደሉም ክፉም ነገሮች አሉት፡፡ ስለዚህ መደመር ለኢትዮጵያ መልካም የፖለቲካ ምህዳሩን ይጠቀማል የተሰሩ ስህተቶቸን ያርማል ከዛም ለቀጣዩ ትውልድ ጥቅም ያካብታል፡፡

በመደመር ውስጥ ሌላው ትልቁ ነጥብ ትብብርና ፉክክር ሚዛናዊ መሆን አለባቸው ብሎ ያምናል፡፡ ፉክክር መኖሩ አስፈላጊ ሆኖ ሳለ ሚዛኑን ስቶ ሀገራዊ ትብብርን መጉዳት የለበትም የሁለቱንም ሚዛን መጠበቅ ተገቢ ነው ብሎ ያምናል፡፡ 

አንድ ሰው ለመደመር ተነሳሽነት (አያገባኝም፣ አይመለከተኝም ከማለት መቆጠብ)፣ ሚዛን መጠበቅ(በትብብርና በመፉክክር መሀል)፣ ግብ(ህብረ-ብሔራዊ አንድነት፣የዜጎች ክብር፣ ብልጽግና) አስፈላጊ ናቸው፡፡ ለመደመር መሰናክሎቹ ተብለው የሚቀመጡት ዋልታ ረገጥነት፣ አቅላይነት፣ ሞያን መናቅ፣ እንቢተኝነት፣ ህሊና ቢስነት ወዘተ ናቸው፡፡

አቶ ዮናስ ዘውዴ ዛሬ በአዲስ ወግ ውይይት ላይ ካቀረቡት ተቀንጭቦ የተወሰደ!

#TIKVAH_ETHIOPIA

PHOTO: EPA

@tsegabwolde @tikvahethiopia


Report Page