#ETH

#ETH


የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ምርጫ ሂደት የህዝቦችን አብሮነት መሰረት ባደረገ መልኩ ማድረግ እንደሚገባ ተገለፀ!

የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስዳተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው በጽሕፈት ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣው መግለጫ የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ምርጫ ሂደት የህዝቦችን አብሮነትን መሰረት ባደረገ መልኩ ማድረግ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የደቡብ ክልል በመረጋጋት ላይ እንደሆነ ርዕሰ መስዳተድሩ ገልፀው ክልሉ እንዲረጋጋ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የክልሉ ህዝብና የጸጥታ መዋቅር ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በጽሕፈት ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣው መግለጫ የመዋቅር ጥቄዎች በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ ዞኖች መጠየቁን አንስተዋል፡፡

ይህም የህዝብ ጥያቄ ምላሽ በወቅቱ አልተመለሰም የሚል ሀሳብ እንዳለ ገልፀው የህዝቦች ጥያቄ ሳይንሳዊ በሆነ ሂደት የሁሉንም ህዝቦች ጥቅም ባገናዘበ ሁኔታ ምላሽ እንደሚያገኝ፤ የመዋቅር ጥያቄዎችም የህዝቦችን አንድነት በማይሸረሽር መልኩ ጊዜ ተወስዶ ምላሽ መስጠት ተገቢ ነው ብለዋል፡፡

በቅርቡ በተደረገው የክልል ምክር ቤት ጉባኤ ላይ የህዝቦች ጥያቄ እንደታፈነ ተደርጎ በአንዳንድ አካላት የሚገለጹት መረጃን መሰረት ያላደረጉ መሆንን ተናገረው ማንኛውንም የህዝቦች ጥያቄ በወቅቱ መመለስ የክልሉ መንግስት አቋም እንደሆነ ጠቁመዋለ፡፡

ርዕሰ መስተዳደሩ በስፋት ያነሱት የሲዳማ ህዝብ ውሳኔን በተመለከተ ሲሆን የህዝበ ውሳኔ ውጤት ምንም ይሁን ምን የህዝቦችን አብሮነት መሰረት ባደረገ መልኩ ማካሄድ እንደሚገባ ተናገረዋል፡፡ የሲዳማ ህዝበ ውሰኔ ምርጫ ሂደት ሰላማዊ ፍትሀዊና ተአማኒነት ያለው እንዲሆን ክልሉ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡

የክልሉ ምክር ቤት ጉባኤ በሰጠው እውቅና መሰረት የደቡብ ክልልን ለሁለት የምርጫ ዘመን መቀመጫውን ሀዋሳ ከተማ እንደሚሆንና የንብረት ክፍፍልም የህዝቦችን አንድነት በማይሸረሽር መልኩ የተረጋጋ ሂደት ተከትሎ ይደረጋል ብለዋል፡፡

የደቡብ ክልል ምክር ቤት ሲዳማ ክልል እንዲሆን ውሳኔ አስተላልፏል የሚሉ መረጃን መሰረት ያላደረጉ ሀሳቦች ይሰማሉ፡፡ ይህም ምክር ቤቱ ከህዝበ ውሳኔ በፊት ምርጫ ቦርድ የጠየቃቸውን ጥያቄዎችን እውቅና እንዲኖረው ተደረገ አንጂ የሲዳማ የክልልነት ጥቄያ ምላሽ የሚያገኘው በቀጣይ በሚደረገው በህዝበ ውሳኔ ምርጫ እንደሆነ አስገንዝበዋል፡፡

ከጋዜጠኞች የተለያዩ ጥያቄዎች የተጠየቁ ሲሆን የኮማንድ ፖስቱ ከአካባቢው ሳይወጣ ምርጫ ማካሄድ እንዴት ይቻላል? የክልል መንግስት በምን ህዝበ ውሳኔ ለማስፈፀም ዝግጁቱ በምን ደረጃ ላይ ነው? እና ሌሎች ተያያዥ ጥያቆዎች ቀርቦላቸው ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ኮማንድ ፖስት የክልሉን ሰላም ለማስጠበቅ ከፍተኛ ሚና እንደነበው ገልጸው ላደረጉት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ኮማንድ ፖስቱ በሀገር ደረጃ ተደራራቢ ተልዕኮ ያለው በመሆኑ በክልሉ ሙለ በሙሉ ሰላም መሰፈኑ ሲረጋገጥ እንደሚወጣ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

የክልል መንግስት ምርጫ ቦርድ የጠየቀውን ቅደመ ሁኔታ ባሟላ መልኩ ምላሽ በመሰጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን የራሱን ድርሻ በተገቢው እንደሚወጣና የህዝቦችን አብሮነት ባገናዘበ መልኩ እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ሚዲዎችም የህዝቦችን አንድነት መሰረት ባደረገ መልኩ መስራት እንደሚጠበቅባቸው ጠቁመዋል፡፡

Via SRTA

Report Page