#ETH

#ETH


ኢ-መደበኛ በሆነ መንገድ በተለይም በክልሎች በራሳቸው የፖሊስን ስራ የሚሰሩና ለህብረተሰቡ ስጋት የሆኑ ወጣቶች መኖራቸው በየመገናኛ ብዙሃኑ ይነገራል። መንገድ በመዝጋት፣ መኪና አስቁሞ በመፈተሽ፣ ይሄ የኛ ነው ያ ያንተ አይደለም የሚል ክልከላ በማድረግ ስጋት የሚፈጥሩ እንዳሉም ህብረተሰቡ ይናገራል። እንድህ ያለውን ህገወጥ አሰራር ለማስተካከል የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ምን እየሰራ ነው?

በኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ጀይላን አብዲ የተጠቀሰውን መሳይ ተግባር የሚፈፅሙ ወጣቶች ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው በፖሊስ ኮሚሽኖች መድረክ ላይ ስምምነት ተደርሶ ለክልሎችም ትዕዛዝ ተሰጥቷል ብለዋል።


"...ስጋት ውስጥ ይከታል የመንግስትን ስምም ያጠፋል፤ ይሄ መስመር መያዝ አለበት ተብሎ ነው ቀጥታ የተቀመጠው። መስመር እንዴት ይይዛል ለሚለው ህጋዊ መሰረት ይዞ እውቅና ተሰጥቶት ከፖሊስ ጋር በበጎ ፍቃደኝነት ከፓሊስ ጋር ወንጀልን ለመከላከል የሚሰሩ ከሆነ እነሱ በዚህ መስመር እንዲቀጥሉ ነው። በራሳቸው ግን ፖሊስን ተክተው መስራት እንደማይችሉ በግልጽ ይነገራቸዋል። የግንዛቤ እጥረትም ካለ ይነገራቸው ነው። ያ ካልሆነና ይሄንን የማይተው ከሆነ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ነው የተቀመጠው አቅጣጫ። ዛሬ እዚህ መስቀል አደባባይ ኢሬቻ ላይ የፈተሸው፤ መስቀል ላይ የፈተሸው በየመንደሩ ይፈትሻል ማለት አይደለም። እስከዛ ድረስ እውቅና አልተሰጠውም። ለዚህ ዝግጅት ብቻ እንዲያግዝ እንዲተባባር ነው። ትራፊክ ፖሊስ ላይ እንደሚደረገው አይነት ሰው እንዲያልፍ፣ መኪና እንዲያልፍ የሚሰሩ ወጣቶች ይደግፋሉ ግን በየቦታው በየፖሊስን ስራ ወስጄ አደባባይም ሰርቻለሁ በየቤቴም፣ ሰፈርም ሰራለሁ ብሎ ቢመጣ ወንጀል ነው። አሁን ግርግር ውስጥ ነው ያለነው መስመር ይይዛል ከትንሽ ጊዜ በኃላ። ይሄ መስመር ይይዛል ስራውን መስራት ያለበት ፖሊስ ብቻ ነው።"

ምንጭ፦ ሸገር FM 102.1 /ትዕግስት ዘሪሁን/

@tsegabwolde @tikvahethiopia

Report Page