#ETH

#ETH


9ኛው ለዛ ሽልማት አሸናፊዎች እና የድምፅ አሰጣጥ ሂደት! 

የአመቱ ምርጥ ነጠላ ዜማ ይህ ዘርፍ ሙሉ በሙሉ በአድማጭ ተመልካች በተሰበሰበ ድምፅ የተወሰነ ሲሆን በዚህም መሰረት ጃንቦ ጆቴ "በልባ" በተሰኝ ነጠላ ዜማ ማሸነፍ ችሏል።

የአመቱ ምራጥ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራም ተዋናይ ዘርፍ ሙሉ በሙሉ በተመልካች በተሰበሰብ ድምፅ የተወሰነ ሲሆን በዚህ መሰረት አበበ ባልቻ(አስናቀ) ከዘመን ድራማ አሸናፊ መሆን ችሏል። 

የአመቱ ምርጥ አዲስ ድምፃዊ ዘርፍ 40% በዳኞች 60% ከአድማጭ ተመልካች በተሰበሰብ ድምፅ የተወሰነ ሲሆን በዚህ ዘርፍ ድምፃዊት ቸሊና ማሸነፍ ችላለች።

የአመቱ ምርጥ ተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማ ተዋናይት ዘርፍ ሙሉ በሙሉ ከተመልካች ድምፅ የተሰበሰብ ሲሆን በዚህ መሰረት አርቲስት ሀና ዮሃንስ ከዘመን ድራማ ማሸነፍ ችላለች።

የአመቱ ምርጥ የሙዚቃ ቪዲዮ ዘርፍ ሙሉ በሙሉ ከተመልካች በተሰበሰበ ድምፅ የተወሰነ ሲሆን በዚህ መሰረት ድምፃዊ ጎሳዬ ተስፋዬ "ከእሁድ እስከ እሁድ" በተሰኝው ቪዲዮ ክሊፕ ማሸነፍ ችሏል። 

የአመቱ ምርጥ ዘፈን ዘርፍ ሙሉ በሙሉ በዳኞች ድምፅ የተወሰነ ሲሆን በዚህም መሰረት በሀይሉ ታፈሰ (ዚጊ ዛጋ) "ሰርካለሜ" በተሰኝው ዘፈን ማሸነፍ ችሏል።

የአመቱ ምርጥ ተዋናይት ዘርፍ 60% የዳኞች ድምፅ 40% በተመልካች ድምፅ የተወሰነ ሲሆን በዚህም መሰረት የምስራች ግርማ በቁራኛዬ ፊልም ማሸነፍ ችላለች። 

የአመቱ ምርጥ ተዋናይ ዘርፍ 60% የዳኞች ድምፅ 40% በተመልካች ድምፅ የተወሰነ ሲሆን በዚህም መሰረት ዘሪሁን ሙላት በቁራኛዬ ፊልም ማሸነፍ ችሏል።

የአመቱ ምርጥ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ዘርፍ ሙሉ በሙሉ በተመልካች በተሰበሰብ ድምፅ የተወሰነ ሲሆን በዚህም መሰረት ፋና ቲቪ ላይ የሚተላለፈው ደርሶ መልስ ድራማ ማሸነፍ ችሏል። 

የአመቱ ምርጥ አልበም ዘርፍ 40% በዳኞች ድምፅ 60% ከአድማጭ ድምፅ ተሰብስቦ የተወሰነ ሲሆን በዚህም መሰረት ቸሊና አሸናፊ መሆን ችላለች። 

የአመቱ ምርጥ ፊልም ዘርፍ 60% በዳኞች ድምፅ 40% በተመልካች ድምፅ ተሰብስቦ የተወሰነ ሲሆን በዚህም መሰረት ቁሯኛዬ ፊልም ማሸነፍ ችሏል።

9ኛው ለዛ ሽላማት ከተዘጋጁት አስራ ሁለት ሽልማቶች ዘርፎች ቁራኛዬ ፊልም ሶስት ሽልማቶችን ዘርፎችን በማሸነፍ ድምፃዊት ቸሊና ሁለት ሽልማት ዘርፎች በማሸነፍ ደምቀው አምሽተዋል። 9ኛው ለዛ ሽልማትም ታሪክ ለመሆን ለ10ኛው ቦታውን ለቋል። 

ቸር ይግጠመን!

@AccessAddis

Report Page