#ETH

#ETH


'ውሁድ ፓርቲ' ለመፍጠር የሚደረገው ጥረት ኢህአዴግን ብቻ ሳይሆን ሀገሪቱም አደጋ ውስጥ የሚያስገባ ተግባር ነው ሲል የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ዛሬ መግለጫ አስታወቀ፡፡ የህዝባዊ ሓርነት ትግራይ ማእከላይ ኮሚቴ ለሰባት ተከታታይ ቀናት ካደረገው ስብሰባ በኋላ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ውሁድ ፓርቲ ለመፍጠር እየተደረገ ያለው ሂደት ሕጋዊነት የጎደለው፣ የሀገሪቱne የፖለቲካ ቀውስ ወደ ባሰ ደረጃ እየገፋ ያለ እንዲሁም ግንባሩንና ሀገሪቱ ወደ መበተን ሊደርስ የሚችል አደጋ ነው ብሎታል። ከቅርብ ግዜ ወዲህ በስመ ውሁድ ፓርቲ እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ ውሁድ የፓርቲ የመፍጠር ሳይሆን አዲስ ፓርቲ የማቋቋም ስራ መሆኑ ጠቅሶ ሕጋዊነት የሚጎደለው ነውም ብሎታል። የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ በመደበኛ ስብሰባው በልማት ስራዎች አፈፃፀም፣ መልካም አስተዳደር፣ የፓርቲና መንግሥት ሥራ አመራር ተግባራት እንዲሁም ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ ላይ መምከሩንም ገልጿል።፡ ማእከላይ ኮሚቴው በመግለጫው ባለፈው ዓመት በአንድ ገፅ ፀረ ድህነት ትግል በሌላ ገፅ ደግሞ 'ትምክህት' ካለው ሀይል ጋር የመከላከል ትግል ሲያደርግ መቆየቱ የገለፀ ሲሆን በፅኑና የሰመረ አንድነት 'ትግሉ' የተሳካ ሆኖ ዘልቋል ብሏል። የትግራይን ህዝብ ፅናትና አንድነት ለመበታተን 'ባንዳ' ያላቸው ኃይሎች የአውራጃና ሃይማኖት አጀንዳ ይዘው እየተንቀሳቀሱ መሆናቸው የጠቆመው የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ መግለጫ፣ አሁንም ህዝቡ 'እንደ ብረት በጠነከረ አንድነቱ' ሊታገላቸው ይገባል ማለቱን ከመቀሌ ዘጋቢያችን ሚሊዮን ኃይለ ሥላሤ በላከልን ዜና ጠቅሷል።  

ከዚህም ሌላ በተያዘው ዓመት ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀው ሀገራዊ ምርጫ በወቅቱ 'የግድ' ሊደረግ ይገባል ያለው ህወሓት እስካሁን ድረስ ቅድመ ዝግጅት ሥራዎች አለመጀመራቸውን ገልፆ ህዝቦች ለመብታቸው ይታገሉ ማለቱ ተገልጿል። ለኤርትራ ህዝብ ባስተላለፈው መልእክትም ባለፈው ዓመት የተጀመረውን የሰላም ሂደት ለማጠናከር እንደሚሰራም አመልክቷል።

Via DW

Report Page