#ETH

#ETH


ህዝቡ ለሀገር ሰላምና አንድነት በጋራ ሊቆም እንደሚገባ የሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን አባገዳዎች አስገነዘቡ ።

በዞኑ የኦዳ ቡሉቅ ኢሬቻ በዓል ትናንት ተከብሯል ።

የኦዳ ቡሉቅ አባ ገዳ ደቻሣ ወዳጆ በስነ ስርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ኢሬቻ የአንድነት፣ የሠላም፣የፍቅርና የወንድማማችነት ተምሳሌት ነው ።

በዓሉ ዘርና ሃይማኖት ሳይለይ ሁሉን በማሳተፍ የሚከበር መሆኑን ተናግረዋል ።

ህዝቡም በዓሉን ሲያከብር በሀገሪቱ ሰላምና አንድነት እንዲሰፍን ፈጣሪውን በመለመንና ለተግባራዊነቱም በጋራ ቃል በመግባት ሊሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።

“ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ የዓለም የኖቤል ሠላም ተሸላሚ በሆኑበት ወቅት በዓሉ መከበሩ ከወትሮው ልዩ ያደርገዋል” ብለዋል።

“በጠቅላይ ሚኒስተሩ የተገኘውን የሰላም ስኬት በማጠናከር ሀገራዊ ለውጡን ማስቀጠል ይገባል”ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል ።

በአባገዳዎች ምርቃት የተጀመረው የበዓሉ አከባበር ስነ ስርዓት በሰላም ተጠናቋል ።

VIA ENA

Report Page