#ETH

#ETH


ግጭቶችንና አለመግባባቶችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የድርሻቸውን እንደሚያበረክቱ በወላይታ ዞን የሶዶ ከተማ ነዋሪ ወጣቶች ገለጹ፡፡ በከተማው በሁለት ወጣቶች መካከል በግል ጸብ መነሻነት የተከሰተው አለመግባባት እንዳይስፋፋ በእርቅ መፈታቱን የዞኑ ወጣቶች ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡

በእርቅ ስነ-ስርዓቱ ላይ የሀገር ሽማግሌዎች በሰጡት አስተያየት ስሜታዊነት ግለሰብን ብቻ ሳይሆን ቤተሰብን፣ አከባቢንና ሀገርን ለጉዳት እንደሚዳርግ ገልጸዋል፡፡ ነገሮችን በሰከነ መንፈስና በመቻቻል ማየት ፍርሀት ሳይሆን አርቆ አስተዋይነት መሆኑን አመላክተው አለመግባባትን በሰላማዊ መንገድ የመፍታት ባህል እንዲሰርጽ ተግተን መስራት አለብን ብለዋል፡፡

የዞኑ ወጣቶች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ወጣት ሚካኤል ዋዳ በሀገራችንና በዞናችን የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ለማፋጠንና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን የሚደረገው ጥረት ከዳር እንዲደርስ የወጣቱ ኃላፊነት ከፍተኛ መሆኑን አመላክቷል፡፡ ወጣቱ ትውልድ ከስሜታዊነት ይልቅ ምክንያታዊነትን በማጎልበት ተጠቃሚነቱን ለማሳደግ ጥረቶቹን አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስቧል፡፡

በወጣቶች መካከል በስሜታዊነት የተፈጠረው አለመግባባት በእርቅና በይቅርታ መፈታቱ አርአያነቱ የጎላ መሆኑን ወጣት ሚካኤል ጠቁሟል፡፡ በእርቁ የተሳተፉ ወጣቶች በሰጡት አስተያየት አለመግባባትን በሰላማዊ መንገድ የመፍታት ባህል ጠቄሜታው ጉልህ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ግጭቶችንና አለመግባባቶችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በቀጣይ የድርሻቸውን እንደሚያበረክቱ ተናግረው ለከተማውና ለሀገራችን ብልጽግናና ሰላም በአብሮነትና በአንድነት መንፈስ እንደንሚንቀሳቀሱ ጠቁመዋል፡፡

Via Wolaita Zone Youth League

@tsegabwolde @tikvahethiopia


Report Page