#ETH

#ETH


#አልማ

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምሥራቅ በለሳ ወረዳ በአማራ አቀፍ ልማት ማኅበር (አልማ) ድጋፍ የተገነቡ ትምህርት ቤቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነዋል። በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ የተገኙት የአልማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ፈንታ ማኅበሩ የሦስት ዓመት ስትራቴጂያዊ ዕቅድ አውጥቶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን በማስታወስ ትምህርት ደግሞ የዕቅዱ ዋነኛ ትኩረት መሆኑን አብራርተዋል።

የሁሉም ነገር ዋስትና ትምህርት መሆኑን የተናገሩት አቶ መላኩ ‹‹የጉሃላ የትምህርት ቤቶች ግንባታ የሙከራ ትግብራ ቅድሚያ የተሰጠውም በወረዳው የሚገኙት ሁሉም ትምህርት ቤቶች ከደረጃ በታች በመሆናቸውና አካባቢውም በልማት ወደ ኋላ የቀረ በመሆኑ ነው›› ብለዋል። የትምህርት ቤቶቹ ግንባታም በሦስት ወራት ጊዜ ውስጥ መጠናቀቅ የአልማን የአፈፃፀም ብቃት ያሳየ እና 'ይቻላል'ን ያረጋገጠ እንደሆነም አስረድተዋል።

የአማራ ክልል ትምሕርት ቢሮ ኃላፊ ይልቃል ከፋለ (ዶክተር) ደግሞ የትምህርት ቤቶች ከደረጃ በታች መሆን የትምህርት ሥርዓቱ ፈተና መሆኑን በመግለፅ ችግሩን ለመፍታትም የጉሃላ የትግበራ ፕሮጀክት ተምሳሌት እንደሆነ አስረድተዋል። ለቀጣይ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ የማሻሻል ፕርጀክቶች ስኬት ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣም ጥሪ አስተላልፈዋል።

Via AMMA


Report Page