#ETH

#ETH


3ኛው የጣና ሽልማት አሸናፊዎች ይፋ ሆነዋል!

በ2011 ዓ.ም ማኅበራዊ የትስስር ገፆችን ለአዕምሮ ሰላምና ለኢትዮጵያዊነት ሲጠቀሙ የነበሩ ግለሰቦችና ድርጅቶች ተለይተዋል። ከ60 በላይ እጩዎች ሲወዳደሩበት በነበረው በዘንድሮው የጣና ሽልማት በ21 ዘርፎች አበርክቶት የነበራቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። በዚህም መሠረት፦

በፈጣን፣ ወቅታዊና ሚዛናዊ መረጃ ዘርፍ- ኤልያስ መሰረት ፣ በባህልና ቱሪዝም ዘርፍ -ቁምነገር ተከተል፣ በስፖር ዘርፍ-ሶከር ኢትዮጵያ፣ በስነ ጥበባዊ ምስሎችና ትርክቶች ዘርፍ- ሀበሻ ሚም፣ በፎቶ ግራፍ ዘርፍ - ኦስማን ካሊፋ፣ በጤና ዘርፍ- ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል፣ በስነ ጽሁፍ ዘርፍ- ተመስገን ባዲሶ፣ በንግድና ቢዝነስ ዘርፍ- "ኢትዮ ጆብስ ቫካንሲ "፣ በበጎ አድራጎትና አካባቢ ልማት ዘርፍ- ስለእናት የበጎ አድራጎት ማህበር፣ ተስፋ በሚጣልበት ወንድ ወጣት ዘርፍ- ዋልተ ንጉስ ዘሸገር፣ ተስፋ በሚጣልባት ሴት ወጣት ዘሮፍ -ሰሎሜ በቃ ዕጹብ፣ በጀማሪ የስነ ፁሁፍ ሰው- ትረካዎች በታዴ፣ በመገናኛ ብዙኃን የማኅበራዊ ሚዲያ ዘርፍ - አማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት፣ በአረንጓዴ ልማት እና አካባቢ ፅዳት - ራስ በረከት አንዳርጌ፣ በሳይንስና ቴክኖሎጅ ዘርፍ - ኢዘዲን ከማል፣ በታሪክ ዘርፍ - ሙሉጌታ አንበርብር ፣ በስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ዘርፍ -አጋላጭ፣ በፈጣን፣ ወቅታዊና ሚዛናዊ መረጃ ቲዩብ - ራማ ሚዲያ፣ በዓመቱ በብዛት የታየ የሙዚቃ ቪዲዮ- ሆፕ ኢንተርቴይመንት - በሠላማዊት ዮሐንስ የሙዚቃ ቪዲዮ፣ በዓመቱ በብዛት የታየ ፊልም - ነፀብራቅ ሚዲያ - በይዋጣልን ፊልም፣ ልዩ ተሸላሚ - ወይዘሮ ሳምራዊት ፍቅሬ - በ ራይድ ናቸው።

አሸናፊዎቹ 30 በመቶ የሚሆነውን ድምጽ ከሕዝብ በተሰጠ ጥቆማና አስተያዬት፣ 70 በመቶ የሚሆነው ደግሞ ከተለያዩ ዘርፎች የተወጣጡ ዳኞች በሰጡት ውጤት መሠረት የተለዩ ናቸው።

እነዚህ ተሸላሚዎች ከጥላቻ ይልቅ ማኅበራዊ አንድነት እንዲጠነክር የሠሩ፣ የሀገራቸውን መልካም ገጽታ ያስተዋወቁና በመሰል አዎንታዊ ተግባራት የተሰማሩ ናቸው። ተሸላሚዎችም ከአንደኛና ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተሻለ ውጤት ካስመዘገቡ ተማሪዎች እጅ ሽልማታቸውን ተቀብለዋል።

ባሕር ዳር ዩኒቨርስቲና ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ በሚያስቀምጡት መስፈርትና ኮታ መሰረት የትምህርት እድል የሚያገኙ ተሸላሚዎች እንዳሉ ተጠቁሟል።

Via AMMA

Report Page