#ETH

#ETH


የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድን የኖቤል ሽልማት ምክኒያት በማድረግ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው መግለጫ፤ "ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ እ.ኤ.አ በ2018 ዓ.ም ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ ለሁለት ዐስርት ዓመታት በኢትዮ ኤርትራ መካከል የነበረውን የድምበር ውዝግብ እልባት በመስጠት ሰላም ማውረድ ችለዋል፡፡ በዚህም ሽልማቱ ተገቢ ነው ብለን እናምናለን፡፡ ይሁን እንጂ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ አሁን ትልቅ ሥራ ይጠብቃቸዋል፡፡ ይህ ሽልማት በአገሪቱ ላይ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጋሬጣ የሆኑ ችግሮችን ለመፍታት ይበልጥ ሊያበረታታቸው ይገባል፡፡" ይላል።

አያይዞም "በአፋጣኝ ሁኔታም በአገሪቱ ውስጥ እየተፈጠረ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና አለመረጋጋት እንዲሁም የብሄር ግጭቶች እልባት መስጠት ይኖርባቸዋል፡፡" ሲል ማሳሰቢያ ይሰጣል። "መንግሥታቸው በአገሪቱ ውስጥ ጫና ለመፍጠር እንደመሳሪያ እያገለገለ ያለውን የጸረ-ሽብር ህጉ በድጋሚ ረቆ እንዲያፀድቅ እና ከዚህ በፊት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ያደረሱ ተጠርጣሪ አካላት ለሕግ እንዲቀርቡ ማድረግ ይኖርበታል፡፡"

የአምነስቲ ኢንተርናሽናል መግለጫ ተከትሎ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የአፍሪቃ ቀንድ በተለይም የኢትዮጵያና የኤርትራ አጥኚ አቶ ፍስሃ ተክሌ የመግለጫውን ይዘት ለአሜሪካ ድምፅ አብራርተዋል።

“ዛሬ ያወጣነው መግለጫ እንደሚያመለክተው የተሰጠው የኖቤል ሽልማት ተገቢ ነው፡፡ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድስልጣን ላይ ከወጡ ጀምሮ የተለያዩ ማሻሻያዎችን አድርገዋል፤ በተለይ ሰብአዊ መብትን በመለከተ አእስረኞች ተለቀዋል የተወሰኑ ህጎችን ተሻሽለዋል የተወሰኑ ህጎችን ለማስተካከል መንገድ ተጀምርዋል ፡፡ከዚህ አልፎ በተለይም ከኤርትራ ጋር ያለው የድንበር አለመግባባት እንዲፈታ ሆኗል፡፡ በሱዳን ሰላም እንዲመጣም እንዲሁ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ነበራቸው፡፡ከዚህ አንጻር ተገቢ ነው እንላለን፡፡ በተለይ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሰብአዊ መብት አንጻር ያሉት ችግሮች ሙሉ ለሙሉ ካለመቀረፋቸው ጋር በተያያዘ ይሄ ሽልማት የበለጠ ያተጋቸዋል ብለን ነው የምናምነው፡፡ከዚህ ቀደም ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመምጣታቸው በፊት የፀረ ሽብር አዋጁ ብዙ የፖለቲካ ተቃዋሚዎችን አክቲቪስቶች የሚባሉትን ፀሃፊዎችን ጋዜጠኞችን ፀጥ ለማስባል መንግስት የሚጠቀምበት ህግ ነበር፡፡ ብዙ ችግር ያለበት ህግ ነው...። ሰልዚህ ቅደሚያ ተሰጥቶት ለሽብር አዋጁ ማስተካከያ አንዲደረግለት እና አለ አግባብ በዚህ ህግ የታሰሩ ሰዎችም በአስቸክዋይ እንዲፈቱ በዚህ አጋጣሚ ለመጠየቅ እንሞክራለን”


አቶ ፍስሃ አክለውም ከዚህ በፊት የተፈጸሙ ከባድ የመብት ጥሰቶች አሉ፡፡ እነዚህ በወንጀል የሚያስጠይቁ ናቸው፡፡ለወንጀሎቹ ሃላፊ የሆኑ ሰዎች እንዲጠየቁ እንዲሁም በየቦታው የሚነሱ ብሄር ተኮር ጥቃቶች እና ግጭቶችን በተመለከተ ዘላቂ መፍትሄ እንዲሰጡ እንፈልጋለን፡፡የጸረ ሽብር አዋጁ ሰዎችን ለማጥቃት እና ጋዜጠኞችን ለማሰር እየዋለ እንደሆነ እያየነው ነው፡፡ይሄም ጉዳይ በዓለም አቀፍ ህግ አግባብ መሰረት እንደሚስተካከል ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል፡፡

VOA

Report Page