#ETH

#ETH


የትራፊክ አደጋ የሰው ህይወት እየቀጠፈ ነው!

በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ፃግብጅ ወረዳ ትናንት ምሽት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን የወረዳው ፖሊስ ፅህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ ረዳት ኢንስፔክተር ጌጡ መሰለ እንደገለፁት አደጋው የደረሰው ከሰቆጣ -ፃታ ሸፌሩን ጨምሮ 19 ሰዎችን አሳፍሮ ይጓዝ የነበረ ኮድ 3-40474 አ.አ ባለ አንድ ጋቤና ላንድ ክሩዘር መኪና በወረዳው ጅልዋ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በመገልበጡ ነው።

በደረሰው አደጋም የአሽከርካሪው እና የአንድ ተሳፋሪ ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ በ18 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል ጉዳት መድረሱን ገልፀዋል፡፡ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ስድስት ሰዎችን ጨምሮ ሌሎች ቀላል ጉዳት የደረሰባቸውተሳፋሪዎች በሰቆጣ ከተማ በሚገኘው የተፈራ ሃይሉ መታሰቢያ ሆስፒታልና በፃታ ጤና ጣቢያ የህክምና እርዳታ እንዲያገኙ ተደርጓል።

የአደጋውን መንስኤ ለማወቅም ፖሊስ በቦታው ተገኝቶ ተገቢውን ምርመራ እያካሄደ መሆኑን ረዳት ኢንስፔክተሩ ተናግረዋል፡፡ የወረዳው ህዝብ መደበኛ የህዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚ ባለመሆኑ ምክንያት በጭነት ተሸከርካሪዎች እየተጓጓዘ መሆኑን የጠቆሙት ሃላፊው ህብረተሰቡ ከአቅም በላይ በሚጭኑ ተሸከርካሪዎች ከመሳፈር እንዲቆጠብ አሳስበዋል፡፡

Via #ENA

@tsegabwolde @tikvahethiopia


Report Page