#ETH

#ETH


በአዲስ አበባና አካባቢዋ ለልማት ሲባል ከቦታቸዉ ለተነሱ አርሶ አደሮች 20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ምትክ እንዲያገኙ የተወሰነው ከወራት በፊት ነው፤ ውሳኔው አዲስ አይደልም ሲል የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ገለፀ።

የኮርፖሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂኒየር ደሳለኝ ተረፈ ለዶቼ ቬለ እንደገለፁት በአዲስ አበባ ዳርቻዎች ይኖሩ የነበሩና ከቦታቸዉ የተነሱ አርሶ አደሮች በ20 / 80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች መርሃ ግብር ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተወሰነው ታህሳስ 24 ቀን፣ 2011 ዓ.ም ነው። ዉሳኔዉ በከተማዉ ካቢኔ መሰሰጠቱን የገለፁት ኃላፊዉ «ይህ ውሳኔ ደግሞ ግንቦት 2011 ዓ.ም ተግባራዊ ተደርጓል። እንደ አዲስ የሚያወዛግብ ነገር አይደለም » ሲሉ ገልፀዋል። ይሁንና ይህ ውሳኔ የሚመለከታቸው ሰዎች ቁጥር ምን ያህል ነው? በሚል ከDW ለተነሳላቸዉ ጥያቄ ኃላፊው፤ «ማህበራዊ መገናኛዎች ላይ የተምታታ ቁጥር አለ፣ ትክክለኛ ቁጥር የለም ቁጥሩንም አልገልፅም » የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ውሳኔው መጀመርያውኑም እጣ ከመውጣቱ በፊት የተወሰነ ነው ያሉት ኃላፊው አሰራሩ የነበረ እና ምትክ 20 / 80 ቤቱ በሁሉም የቤት ግንባታዎች በሚከናወኑባቸው ቦታዎች የሚሰጥ መሆኑን አብራርተዋል።የልማት ተነሽዎቹ በወቅቱ ካሳ አልተከፈላቸዉም ወይ? በሚል ለተነሳላቸዉ ጥያቄ፤ ምላሽ መስጠት ያለበት ሌላ አካል መሆኑን አመልክተዋል። ተነሺ አርሶአደሮቹ በዚህ የቤት መርሃ ግብር ተጠቃሚ ሊሆኑ የቻሉት ግን መንግስት በግልጽ በወሰነው የቆየ አሠራር ነው ብለዋል። ለ20 / 80 የጋራ መኖሪያ ቤት ለዓመታት ቆጥበው እጣ የወጣላቸው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች፣ እስካሁን ወደ ቤታቸው ያልገቡ እድለኞች አሉ፤ ይህስ የት ደረሰ ተብለው የተጠየቁይኃላፊው፦ ጉዳዩ ኮሚቴ ተቋቁሙ እየታየ ነው ብለዋል። በተጨማሪም በሃገር ደረጃ የሚወሰነውን ውሳኔ ተግባራዊ ለማድረግ እየጠበቅን ሲሉ አመልክተዋል።

Via DW

@tsegabwolde @tikvahethiopia

Report Page