#ETH

#ETH


ከሀረር ወደ ጅግጅጋ የሚወስደውና በፌደራል መንገድ ባለስልጣን የሚተዳደረው የመኪና መንገድ ድልድይ በመሰንጠቁ ምክንያት የትራንስፖርት አገልግሎት መቋረጡን አሽከርካሪዎችና ተገልጋዮች ተለፁ።

********************************************

በፌደራል መንገዶች ባለስልጣን የሚተዳደረውና ከሀረር ወደ ጅግጅጋ የሚወስደው የመኪና መንገድ ኤረር ቀበሌ አካባቢ የሚገኘው ድልድይ በመሰንጠቁ አገልግሎት መስጠት በማቋረጡ አሽከርካሪዎችና ተገልጋዮች እየተቸገሩ መሆኑን ተናገሩ።

ከድሬዳዋ ወደ ጎዴ አልሚ የእርዳታ እህል ጭኖ እየተጓዘ ሳለ በመንገዱ መበላሸት ምክንያት በአካባቢው ቆሞ ያገኘንው የከባድ መኪና አሽከርካሪ አቶ ደረጀ የማነህ እንደሚገልፀው አደጋ የደረሰበት ድልድይ በወቅቱ ባለመጠገኑ ለሰባት ቀናት የጫነው እቃ ሳናራግፍ በስፍራው ለመቆየት ተገደናል።

በአካባቢውም የተደራጀ ጥበቃ ባለሞኖሩ ንብረቱ ለስርቆት እየተዳረገ ነው፤ ተሽከርካሪም ለማለፍ ሲሉ ለትራፊክ አደጋ እየተዳረግን ነው ብለዋል፡፡

በአካባቢው የምግብና ውሃ አቅርቦት ባለመኖሩም እየተቸገሩ መሆናቸውን ገልፀው ለዚህ ሁሉ ችግሩ መንገዱ በወቅቱ አለመሰራቱና ተሽከርካሪዎች በስፍራው ላይ መበራከት በመሆኑ መፍትሄ ሊሰጥበት ይገባል ሲል ተሯል።

የነዳጅ ቦቴ አሽከርካሪው አቶ መኮንን ቦጋለ እንደተነገሩት ተለዋጭ መንገዱን ባግባቡ ሰርቶ የሚያሳልፈን ባለመሆ የያዝነውን ጭነት ሳናራግፍ ለእንግልት ተደርገናል ሲሉ ተነግረዋል፡፡

ግማሽ ኪሎ ሜትር የማይሞላ ተወለዋጭ መንገድን በአንድ ቀን መስራት ሲቻል ከጅቡቲ ድረስ ተጉዘን ለህዝብ ማድረስ የሚገባንን ንብረት ሳናደርስና የተሽከርካሪው ባለንብረትና መንግስት ከዘርፉ ሊያገኝ የሚችለውን ገቢ እያጡ ነው።

በርካታ ስፍራዎች ላይ የመንገድ ብልሽት ያጋጥማል ይህን ከልምድ መመልከት ችያለው ወድያውኑ መፍትሄ ሲሰጥ ነው የምናየው ይህ ግን ሁሉም እየተቸገረ ስለሚገኝ መፍትሄ ይሰጥበት ብለዋል።

ነዳጅ የጫኑ ተሽከርካሪዎች በየስፍራውና ሐረር ከተማ ላይ በመቆማቸው የነዳጅ ዋጋ በሶማሌ ክልል ከተሞች ላይ በእጥፍ መጨመሩን የገለጹት የከባድ መኪና አሽከርካሪው አቶ ሲሳይ ጌታቸው መንግስት በጉዳዩ ትኩረት ይስጥበት ሲሉ ተናግረዋል።

መፍትሄ ይገኛል በማለት ያለምንም ስራ በአካባቢውና በሐረር ከተማ ያለ ስራ በመቀመጥ ለተጨማሪ ወጪ መዳረጋቸውንም ገልጸዋል።

በድልድዩ መሰበር ምክንያት ከመኪና ወደ ሌላ መኪና በቅብብሎሽ ሲጉዙ ያገኘናቸው አቶ ይድነቃቸው ሁሴን በመንገዱ መበላሸት ምክንያት ለእንግልት ተዳርገናል፤ የትራንስፖርት ታሪፍ ከእጥፍ በላይ ጨምሯል በቅብብሎሽም ትራንስፖርት እየተጓዝን እንገኛለን።

ድልድዩ 10 ዓመት ሳይሞላው ይህ ነገር መከሰቱ እጅግ ያሳዝናል፤ በተለይ መንግስት መንገዶችንና ድልድዮችን በኮንተራክተሮች ላይ ሲረከብ ጥራቱን መመልከት ይገባዋል በአሁኑ ወቅት የተፈጠረውን ችግር ከጥራት ጋር የተያያዘ በመሆኑ መንግስት ተመልክቶ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

በስልክ ያነጋገርናቸው የፌደራል መንገዶች ባለስልጣን የድሬዳዋ ዲስትሪክት ዳይሬክተር ኢንጅነር ሱራፌል ሚካኤል እንደገለጹት ከአራት ቀናት በፊት በስፍራው የነበሩትን ተሽከርካሪዎች በሙሉ በተለዋጭ መንገድ ወደ ጅግጅጋና ሐረር ድሬዳዋ አሸጋግረናል በአሁኑ ወቅት በቦታው የሚገኙት ትላንትናና ዛሬ የገቡ ተሽከርካሪዎች ናቸው።

ችግሩን ለመቅረፍ በአጭር ጊዜ ከፀጥታ አካላት ጋር ብንሰራም የዝናቡ ሁኔናታ በተለይ ደግሞ የአሽከርካሪዎች ትግስት ማጣት ተለዋጭ መንገዱን ይበልጥ ለተጨማሪ ብልሽት እየዳረገ ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል።

ዋናውን መንገድ በመዝጋትና የኮንቦልቻ ጃርሶ፣ ጭናክሰን መንገድ እንደአማራጭ አሽከርካሪዎች እንዲጠቀሙ በማድረግ በሁለት ቀናት ውስጥ ተለዋጭ መንገዱን ለመስራት እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል።

Via Harari Government communication affairs Office

Report Page