#ETH

#ETH


የታጠቁ አካላት በኤፍራታና ግድም ወረዳ ተኩስ ከፍተው አካባቢውን ለመረበሽ ያደረጉት ሙከራ መክሸፉን የወረዳው አስተዳድርና ፀጥታ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

ለጊዜው ማንነታቸው ያልታወቁ የታጠቁ ኃይሎች በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ ከተራራ ሥፍራ በመሆን ወደ አጣዬ ከተማ በመተኮስ የአካባቢውን ሰላም እየረበሹ መሆኑን የወረዳው አስተዳድርና ፀጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌታቸው የሽጥላ ገልፀዋል።

አቶ ጌታቸው እንዳስታወቁት ከተራራ ወደ ከተማዋው በተከፈተው ተኩስ ስጋት የአጣዬ ቅዳሜ ገበያ ተበትኗል፤ ነዋሪውም እየተረበሸ ነው።

የአማራ ክልል ልዩ ኃይልና የመከላከያ ሠራዊት ሕዝቡን ለማረጋጋት እየሠሩ እንደሆነም ኃላፊው አስታውቀዋል። የታጠቁ ኃይሎቹ በርከት ያሉ መሆናቸውንና በብዙ አቅጣጫ እንደሚተኩሱ ከመግለጻቸው ባለፈ ማንነታቸውና በሰው ላይ ያደረሱት ጉዳት ስለመኖሩ አልተገለጸም።

የሰሜን ሸዋ ዞን የሠላምና ደኅንነት ግንባታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ካሳሁን እምቢያለ ግን የታጠቁ ቡድኖቹ በልዩ ኃይል ላይ ጥቃት ሊፈጽሙ መሞከራቸውንና በአጸፋው ከጥፋት ኃይሎቹ አንዱ መገደሉን አስታውቀዋል። መምሪያው ሁኔታው ወደ መረጋጋት መመለሡንም አስታውቋል። አካባቢውን ልዩ ኃይል፣ ፌዴራል ፖሊስና መከላከያ ሠራዊት መቆጣጠሩም ተብራርቷል።

በኤፍራታና ግድም የተከሰተው ሁኔታ ከሰሞኑ በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አጋጥሞ እንደነበር ከተገለጸው ክስተት ጋር የማይገናኝ ስለመሆኑም የመምሪያው ኃላፊ አስታውቀዋል።

VIA AMMA

Report Page